ሕዝቅኤል 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ያለ ገለባም ለሚመርጉት ሰዎች፦ ይወድቃል በላቸው። የሚያሰጥም ዝናብ ይዘንባል፤ ታላቅም የበረዶ ድንጋይ በራሳቸው ላይ አወርዳለሁ፤ እነርሱም ይወድቃሉ፤ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስም ይሰነጣጥቀዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ስለዚህ በኖራ ለሚለስኑት ካቡ እንደሚወድቅ ንገራቸው። ዶፍ ይወርዳል፤ ታላቅ የበረዶ ድንጋይ እሰድዳለሁ፤ ዐውሎ ነፋስም ይነሣል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በኖራ የሚቀቡትን እንዲህ በላቸው፦ ይወድቃል፤ ዶፍ ዝናብ ይዘንባል፥ ታላቅም የበረዶ ድንጋዮች ይወድቃሉ፥ ዐውሎ ነፋስም ይሰነጣጥቀዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ዶፍ ዝናብ ይዘንባል ታላቅ የበረዶ ድንጋዮች ይወርዳሉ፤ ዐውሎ ነፋስም ይነሣል፤ ስለዚህ ግድግዳውን ቀለም ለቀቡ ሰዎች ግድግዳው ይወድቃል በላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ገለባ በሌለበት ጭቃ ይመርጉታልና ገለባ በሌለበት ጭቃ ለሚመርጉት ሰዎች፦ ይወድቃል በላቸው። የሚያሰጥም ዝናብ ይዘንባል፥ ታላቅም የበረዶ ድንጋይ ይወድቃል፥ ዐውሎ ነፋስም ይሰነጣጥቀዋል። 参见章节 |