Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 12:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሰዎች የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸው ከተ​ሞች ይጠ​ፋሉ፤ ምድ​ሪ​ቱም ውድማ ትሆ​ና​ለች፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሰው ይኖርባቸው የነበሩ ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ ምድሪቱም ወና ትሆናለች። በዚያ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ይጠፋሉ፥ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 አሁን በሕዝብ ተሞልተው የሚታዩ ከተሞች ይጠፋሉ፤ አገሪቱም ምድረ በዳ ትሆናለች፤ በዚያን ጊዜ እነርሱ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ባድማ ይሆናሉ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 12:20
23 交叉引用  

ከተ​ሞ​ችም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ ቤቶ​ችም ባዶ ሆነው ይቀ​ራሉ፤ ይጠ​ፋ​ሉም።


እነሆ፥ ምድር መፈ​ታ​ትን ትፈ​ታ​ለች፤ ፈጽ​ማም ትበ​ረ​በ​ራ​ለች፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ዲህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


የጌ​ጦ​ች​ሽም ሣጥ​ኖች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ይዋ​ረ​ዳ​ሉም፤ ብቻ​ሽ​ንም ትቀ​ሪ​ያ​ለሽ፤ ከም​ድ​ርም ጋር ትቀ​ላ​ቀ​ያ​ለሽ።”


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በዘ​መ​ና​ች​ሁም የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


እን​ዲ​ህም ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ የሸ​ክላ ማድጋ እን​ደ​ሚ​ሰ​ባ​በር ደግ​ሞም ይጠ​ገን ዘንድ እን​ደ​ማ​ይ​ቻል፥ እን​ዲሁ ይህን ሕዝ​ብና ይህ​ችን ከተማ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ የሚ​ቀ​በ​ሩ​በ​ትም ስፍራ ሌላ የለ​ምና በቶ​ፌት ይቀ​በ​ራሉ።


እነሆ ልኬ የሰ​ሜ​ንን ወገ​ኖች ሁሉ፤ ባሪ​ያ​ዬ​ንም የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆ​ርን እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ በዚ​ችም ምድ​ርና በሚ​ቀ​መ​ጡ​ባ​ትም ሰዎች ላይ፥ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ባሉ በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ፈጽ​ሜም አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ለጥ​ፋ​ትና ለፉ​ጨት ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ዕፍ​ረት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እነሆ እኔ አዝ​ዛ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ወደ​ዚ​ህ​ችም ሀገር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ይወ​ጋሉ፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ የይ​ሁ​ዳ​ንም ከተ​ሞች ሰው የሌ​ለ​በት ባድማ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


አን​በሳ ከጕ​ድ​ጓዱ ወጥ​ቶ​አል፤ አሕ​ዛ​ብ​ንም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው የሚ​ዘ​ርፍ ተነ​ሥ​ቶ​አል፤ ምድ​ር​ሽን ባድማ ያደ​ርግ ዘንድ፥ ከተ​ሞ​ች​ሽ​ንም ሰው እን​ዳ​ይ​ኖ​ር​ባ​ቸው ያፈ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ ከስ​ፍ​ራው ወጥ​ቶ​አል።


የጽ​ዮን ተራራ ባድማ ሆና​ለ​ችና፥ ቀበ​ሮ​ዎ​ችም ተመ​ላ​ል​ሰ​ው​ባ​ታ​ልና።


በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል በም​በ​ት​ና​ቸው ጊዜ፥ በሀ​ገ​ሮ​ችም በም​ዘ​ራ​ቸው ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካ​ከል ያለ​ውን የወ​ይን ግንድ እሳት ይበ​ላው ዘንድ እንደ ሰጠ​ሁት፥ እን​ዲሁ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ።


ዐመ​ፅን አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ምድ​ሪ​ቱን ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ለቀ​ሩት አሕ​ዛብ ርስት ትሆኑ ዘንድ በዙ​ሪ​ያ​ችሁ ያሉ አሕ​ዛብ አዋ​ር​ደ​ዋ​ች​ኋ​ልና፤ ውጠ​ዋ​ች​ሁ​ማ​ልና፥ እና​ን​ተም የተ​ና​ጋ​ሪ​ዎች ከን​ፈር መተ​ረ​ቻና የአ​ሕ​ዛብ ማላ​ገጫ ሆና​ች​ኋ​ልና፤


በዙ​ሪ​ያ​ሽም በአሉ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል በሚ​ያ​ል​ፉም ሁሉ ፊት ከል​ጆ​ችሽ ጋር አጠ​ፋ​ሻ​ለሁ።


ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁ​ንም ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ች​ሁ​ንም አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁ​ንም መዓዛ አላ​ሸ​ት​ትም።


እና​ን​ተ​ንም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ትም ሁሉ ሰይፍ ታጠ​ፋ​ች​ኋ​ለች፤ ምድ​ራ​ች​ሁም የተ​ፈ​ታች ትሆ​ና​ለች፤ ከተ​ሞ​ቻ​ች​ሁም ባድማ ይሆ​ናሉ።


跟着我们:

广告


广告