Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያ ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ፥ በእስራኤልም ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህም በገዛ አገራችሁ ድንበር ላይ በጦርነት ትገደላላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ በእስራኤልም ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 11:10
15 交叉引用  

በዚ​ያም ዘመን ሰሎ​ሞን፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከኤ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ግብፅ ወንዝ ድረስ ያለው ታላቅ ጉባኤ፥ እርሱ በሠ​ራው ቤት ውስጥ በአ​ም​ላ​ካ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፥ ደስ​ታም እያ​ደ​ረጉ ሰባት ቀን በዓ​ሉን አከ​በሩ።


በጋ​ት​ሔ​ፌር በነ​በ​ረው በአ​ማቴ ልጅ በባ​ሪ​ያው በነ​ቢዩ በዮ​ናስ አፍ እንደ ተና​ገ​ረው እንደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድን​በር ከሔ​ማት መግ​ቢያ ጀምሮ እስከ ዓረባ ባሕር ድረስ መለሰ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍር​ድን ማድ​ረግ ያው​ቃል፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛው በእ​ጆቹ ሥራ ተጠ​መደ።


የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስን ልጆች በዐ​ይኑ ፊት በዴ​ብ​ላታ ገደ​ላ​ቸው፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ የይ​ሁ​ዳን ታላ​ላ​ቆች ሁሉ ገደለ።


ነገር ግን የሚ​መ​ካው፦ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን፥ ጽድ​ቅ​ንም በም​ድር ላይ የማ​ደ​ርግ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሆ​ኔን በማ​ወ​ቁና በማ​ስ​ተ​ዋሉ በዚህ ይመካ፤ ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘኝ ይህ ነውና፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ያለ ገለባ የመ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ት​ንም ቅጥር አፈ​ር​ሳ​ለሁ፤ ይወ​ድ​ቃል፤ ወደ ምድ​ርም እጥ​ለ​ዋ​ለሁ፤ መሠ​ረ​ቱም ይታ​ያል፤ እር​ሱም ይና​ዳል፤ በመ​ካ​ከ​ሉም ትጠ​ፋ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ሽፋ​ኖ​ቻ​ች​ሁን ደግሞ እቀ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ሕዝ​ቤ​ንም ከእ​ጃ​ችሁ አድ​ና​ለሁ፤ ከዚ​ያም ወዲያ በእ​ጃ​ችሁ ለመ​ታ​ደን አይ​ሆ​ኑም፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


ስለ​ዚህ፥ ሐሰ​ትን አታ​ዩም፤ እን​ግ​ዲ​ህም ከንቱ ምዋ​ር​ትን አታ​ም​ዋ​ር​ቱም፤ ሕዝ​ቤ​ንም ከእ​ጃ​ችሁ አድ​ና​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”


እጄም ሐሰ​ተኛ ራእ​ይን በሚ​ያዩ፥ ሕዝ​ቤ​ንም ለማ​ታ​ለል በከ​ንቱ በሚ​ያ​ም​ዋ​ርቱ ነቢ​ያት ላይ ትሆ​ና​ለች። እነ​ር​ሱም በሕ​ዝቤ ማኅ​በር ውስጥ አይ​ኖ​ሩም፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት መጽ​ሐፍ አይ​ጻ​ፉም፥ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አይ​ገ​ቡም፤ እኔም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


ሙታ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይወ​ድ​ቃሉ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ያለው የጌ​ባ​ላ​ው​ያን ምድር ሁሉ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ከአ​ር​ሞ​ን​ዔም ተራራ በታች ካለ​ችው ጌል​ገላ ጀምሮ እስከ ኤማት መግ​ቢያ ድረስ ያለ​ችው ሊባ​ኖስ ሁሉ፥


跟着我们:

广告


广告