Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ፤ እኔም እያ​የሁ ከም​ድር በረሩ፤ በወ​ጡም ጊዜ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ፊት ለፊት በአ​ለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ በር ዳርቻ ቆሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር ከእ​ነ​ርሱ ጋራ በላ​ያ​ቸው ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኪሩቤልም እኔ እያየኋቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ከምድር ተነሥተው ሄዱ፤ መንኰራኵሮቹም ዐብረዋቸው ሄዱ፤ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ላይ ቆሙ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ እኔም እያየሁ ከምድር ተነሡ፥ ሲወጡም መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በጌታ ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ላይ ነበረ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኔም ይህን በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው ከመሬት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ከጐናቸው የነበሩትም መንኰራኲሮቹ አብረዋቸው ሲወጡ አየሁ፤ በቤተ መቅደሱ በስተ ምሥራቅ ባለው የቅጽር በር ሲደርሱ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክም ክብር በእነርሱ ላይ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ እኔም እያየሁ ከምድር ከፍ ከፍ አሉ፥ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 10:19
9 交叉引用  

እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም በኪ​ሩ​ቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላ​ያ​ቸው እንደ ሰን​ፔር ድን​ጋይ ያለ ዙፋን የሚ​መ​ስል መልክ ተገ​ለጠ።


መን​ፈ​ስም አነ​ሣኝ፤ ወደ ምሥ​ራ​ቅም አን​ጻር ወደ​ሚ​ያ​ሳ​የው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ወሰ​ደኝ። እነ​ሆም በበሩ መግ​ቢያ ሃያ አም​ስት ሰዎች ነበሩ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም የሕ​ዝ​ቡን አለ​ቆች የዓ​ዙ​ርን ልጅ ያእ​ዛ​ን​ያ​ንና የበ​ና​ያስ ልጅ ፈላ​ጥ​ያን አየሁ።


ወደ ምሥ​ራ​ቅም ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር አመ​ጣኝ።


እነ​ሆም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ክብር ከም​ሥ​ራቅ መን​ገድ መጣ፤ ድም​ፁም እንደ ብዙ ውኆች ይተ​ምም ነበር፤ ከክ​ብ​ሩም የተ​ነሣ ምድር ታበራ ነበር።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ወደ ምሥ​ራቅ በሚ​መ​ለ​ከት በር ወደ መቅ​ደሱ ገባ።


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ውስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ መግ​ቢያ ፊት በወ​ለ​ሉና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ሃያ አም​ስት የሚ​ያ​ህሉ ሰዎች ነበሩ፤ ጀር​ባ​ቸ​ውም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መቅ​ደስ፥ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ምሥ​ራቅ ነበረ፤ እነ​ር​ሱም ወደ ምሥ​ራቅ ለፀ​ሐይ ይሰ​ግዱ ነበር።


跟着我们:

广告


广告