ሕዝቅኤል 10:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ሲሔዱም በአራቱ ጎድናቸው ይሄዱ ነበር። ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር፤ መጀመሪያው ወደሚያመለክትበት ስፍራ ይሄዱ ነበር፤ ሲሄዱም ወዲያና ወዲህ አይሉም ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 መንኰራኵሮቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜም ኪሩቤል ወደ ዞሩበት ወደ አራቱ አቅጣጫ ሁሉ መሄድ ይችሉ ነበር፤ ኪሩቤል በሚሄዱበት ጊዜ መንኰራኵሮቹ ወዲያ ወዲህ አይሉም ነበር፤ ኪሩቤል በሚሄዱበት ጊዜ ወዲያ ወዲህ ሳይሉ፣ ራስ ወደ ዞረበት ወደ ማንኛውም አቅጣጫ ይጓዙ ነበር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ሲሄዱም በአራቱም ጎናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም ነበር፥ ራስ ወደዞረበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም ነበር። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ወደ ፊታቸው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሳይዞሩ በቀጥታ ይሄዳሉ፤ የፊቱ መንኰራኲር ወደ የትኛውም አቅጣጫ ቢሄድ ሌሎቹ ሳይዞሩ በቀጥታ ይከተላሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ሲሄዱም በአራቱ ጐድናቸው ይሄዱ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር፥ ራሱ ወደምታመለክትበት ስፍራ ወደዚያ ይከተሉ ነበር፥ ሲሄዱም አይገላመጡም ነበር። 参见章节 |