Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስመ​ለ​ከ​ትም፥ እነሆ በአ​ራቱ እን​ስ​ሶች አጠ​ገብ በም​ድር ላይ አንድ መን​ኰ​ራ​ኵር አየሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሕያዋን ፍጡራኑን ስመለከታቸው፣ አራት ፊቶች ባሉት በእያንዳንዱ ፍጡር አጠገብ አንዳንድ መንኰራኵር በምድር ላይ አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሕያዋኑንም ስመለከት፥ እነሆ፥ በአራቱ ሕያዋን አጠገብ በምድር ላይ ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ መንኰራኵር አየሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አራቱን ፍጥረቶች በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ አራት መንኰራኲሮች ወደ መሬት ተሽከርክረው ሲወርዱና በሕያዋን ፍጥረቶቹ አጠገብ ጐን ለጐን በተርታ ሲቀመጡ አየሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንስሶችንም ስመለከት፥ እነሆ፥ በአራቱ እንስሶች አጠገብ በምድር ላይ አንድ አንድ መንኰራኵር አየሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:15
9 交叉引用  

በየ​መ​ቀ​መ​ጫ​ዎ​ቹም ሁሉ አራት የናስ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ነበ​ሩ​ባ​ቸው፤ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም የሚ​ዞ​ሩ​በ​ትን የናስ ወስ​ከ​ምት ሠራ፤ ከመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውም ሰን በታች በአ​ራቱ ማዕ​ዘን በኩል አራት በም​ስል የፈ​ሰሱ እግ​ሮች ነበሩ።


ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ፊት፥ ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም አራት አራት ክንፍ ነበ​ሩት።


በፍ​ታም የለ​በ​ሰ​ውን ሰው፥ “በመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች መካ​ከል በኪ​ሩብ በታች ግባ፤ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል ከአ​ለው እሳት ፍም እጆ​ች​ህን ሙላ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ላይ በት​ነው” ብሎ ተና​ገ​ረው። እኔም እያ​የሁ ገባ።


እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም በኪ​ሩ​ቤል አጠ​ገብ አራት መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ነበሩ፤ አንዱ መን​ኰ​ራ​ኵር በአ​ንዱ ኪሩብ፥ አንዱ መን​ኰ​ራ​ኵር በአ​ንዱ ኪሩብ አጠ​ገብ ነበረ። የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መልክ እንደ ቢረሌ ድን​ጋይ ነበረ።


የእ​ነ​ዚ​ያም እን​ስሳ ክን​ፎች እርስ በር​ሳ​ቸው ሲማቱ፥ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸ​ውም የመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ችን ድምፅ፥ የታ​ላ​ቁ​ንም ንው​ጽ​ው​ጽታ ድምፅ ሰማሁ።


ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል፤ ሁለተኛውም እንስሳ ጥጃን ይመስላል፤ ሦስተኛውም እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው፤ አራተኛውም እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል።


跟着我们:

广告


广告