ዘፀአት 9:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በዚያ ጊዜም በግብፃውያን ከብቶችና በእስራኤል ልጆች ከብቶች መካከል ልዩነት አደርጋለሁ። ከእስራኤልም ልጆች ከብቶች አንዳች አይሞትም።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ነገር ግን እግዚአብሔር በእስራኤልና በግብጽ እንስሳት መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ይኸውም የእስራኤል የሆነ ማንኛውም እንስሳ እንዳይሞት ነው።’ ” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ጌታም በእስራኤልና በግብጽ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አይሞትም።’” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 እግዚአብሔር ግን በእስራኤላውያንና በግብጻውያን እንስሶች መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አይሞትም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 እግዚአብሔርም በእስራኤልና በግብፅ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንዳች አይጠፋም።’” 参见章节 |