Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 9:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ከከ​ተማ ወጣ፤ እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘረጋ፤ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም፥ በረ​ዶ​ውም ጸጥ አለ፤ ዝና​ቡም በም​ድር ላይ አላ​ካ​ፋም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ከዚያም ሙሴ ከፈርዖን ተለይቶ ከከተማው ወጣ። እጁን ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ቆመ፤ ዝናቡም በምድሪቱ ላይ መዝነቡን አቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፥ እጁንም ወደ ጌታ ዘረጋ፤ ነጎድጓዱም በረዶውም ቆመ፥ ዝናቡም ወደ ምድር አልዘነበም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ሙሴ ከንጉሡ ፊት በመውጣት ከከተማው ውጪ ሄደ፤ እጁንም ዘርግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ዝናቡም በአንድ ጊዜ ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ከከተማ ወጣ፤ እጁንም ወደ እግዚአብሔር ዘረጋ፤ ነጎድጓዱም በረዶውም ተቍረጠ፤ ዝናቡም በምድር ላይ አልፈሰሰም።

参见章节 复制




ዘፀአት 9:33
8 交叉引用  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጉባኤ ሁሉ እያዩ ሰሎ​ሞን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ፊት ቆሞ እጆ​ቹን ወደ ሰማይ ዘረጋ።


ሙሴና አሮ​ንም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጡ፤ ሙሴም ፈር​ዖን እንደ ቀጠ​ረው ሰለ ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ መራቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም።


ስን​ዴ​ውና አጃው ግን አል​ተ​መ​ቱም፤ ገና ቡቃያ ነበ​ሩና።


ፈር​ዖ​ንም ዝናቡ፥ በረ​ዶ​ውም፥ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም ጸጥ እንደ አለ በአየ ጊዜ በደ​ልን ጨመረ፤ እር​ሱና ሹሞ​ቹም ልባ​ቸ​ውን አደ​ነ​ደኑ።


跟着我们:

广告


广告