ዘፀአት 9:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 በረዶውም በግብፅ ሀገር ሁሉ በሜዳ ያለውን ሁሉ ሰውንና እንስሳን መታ፤ በረዶውም የእርሻን ቡቃያ ሁሉ መታ። የጫካውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 በመላው ግብጽ በረዶ በመስክ ላይ ያለውን ሁሉ፣ ሰዎችንና እንስሳትንም መታ፤ በመስክ ላይ የበቀለውን ሁሉ አጠፋ፤ ዛፉን ሁሉ ባዶ አስቀረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 በረዶውም በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ ያለውን ሁሉ ከሰው እስከ እንስሳ መታ፤ የእርሻን ቡቃያ መታ፥ በረዶውም የአገሩን ዛፍ ሁሉ ሰበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 በረዶው በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ሕዝቡንና እንስሶቹን ጭምር ጨፈጨፈ፤ በሜዳ ላይ ያለውን አትክልት ሁሉ መታ፤ ዛፎችንም ሁሉ ሰባበረ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 በረዶውም በግብፅ አገር ሁሉ በሜዳ ያለውን ሁሉ ሰውንና እንስሳን መታ፤ በረዶውም የእርሻን ቡቃያ ሁሉ መታ፤ የአገሩንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ። 参见章节 |