Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ፈር​ዖ​ንም ጸጥታ እንደ ሆነ በአየ ጊዜ ልቡ ደነ​ደነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ፈርዖን ችግሩ ጋብ ማለቱን ባየ ጊዜ ግን ልክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ልቡን በማደንደን ሙሴንና አሮንን አልሰማቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አስማተኞቹም ፈርዖንን፦ “ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈርዖን ልብ ግን ደነደነ፥ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ንጉሡ ጓጒንቸሮቹ መሞታቸውን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳለው ልቡን አደንድኖ አልሰማቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:15
24 交叉引用  

ሕዝ​ቡም እንደ ኰበ​ለሉ ለግ​ብፅ ንጉሥ ነገ​ሩት፤ የፈ​ር​ዖ​ንና የሹ​ሞ​ቹም ልብ በሕ​ዝቡ ላይ ተለ​ወ​ጠና፥ “እን​ዳ​ይ​ገ​ዙ​ልን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የለ​ቀ​ቅ​ነው ምን ማድ​ረ​ጋ​ችን ነው?” አሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


ፈር​ዖ​ንም አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጄ​ንም በግ​ብፅ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሕዝ​ቤን በኀ​ይሌ በታ​ላቅ ፍርድ ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ለሁ።


እንደ ክም​ርም አድ​ር​ገው ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ምድ​ርም ገማች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን በእ​ጅህ ዘርጋ፤ የም​ድ​ሩ​ንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማ​ልም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ይወ​ጣል።”


ፈር​ዖ​ንም፥ “ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በም​ድረ በዳ ትሠዉ ዘንድ እለ​ቅ​ቃ​ች​ኋ​ለሁ፤ ነገር ግን በጣም ርቃ​ችሁ አት​ሂዱ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጸል​ዩ​ልኝ” አለ።


ሙሴም፥ “እነሆ፥ ከአ​ንተ ዘንድ እወ​ጣ​ለሁ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጸ​ል​ያ​ለሁ፤ የውሻ ዝን​ቡም ከአ​ንተ፥ ከሹ​ሞ​ች​ህና ከሕ​ዝ​ብህ ነገ ይር​ቃል፤ ነገር ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዉ ዘንድ ሕዝ​ቡን እን​ደ​ማ​ት​ለ​ቅቅ እን​ደ​ገና ማታ​ለ​ልን አት​ድ​ገም።”


ፈር​ዖ​ንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደ​ነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።


ፈር​ዖ​ንም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ጠርቶ፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹን ከእኔ፥ ከሕ​ዝ​ቤም እን​ዲ​ያ​ርቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ዩ​ልኝ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይሠዋ ዘንድ ሕዝ​ቡን እለ​ቅ​ቃ​ለሁ” አላ​ቸው።


ክፉን ከሚ​ያ​ደ​ርጉ ወገን ፈጥኖ ክር​ክ​ርን የሚ​ያ​ደ​ርግ የለ​ምና፤ ስለ​ዚህ የሰው ልጆች ልብ በእ​ነ​ርሱ ክፉን ለመ​ሥ​ራት ጠነ​ከረ።


በም​ድር ጽድ​ቅን የማ​ይ​ማ​ርና መል​ካ​ምን የማ​ያ​ደ​ርግ ኃጥእ አል​ቆ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር እን​ዳ​ያይ ኀጢ​አ​ተ​ኛን ያስ​ወ​ግ​ዱ​ታል።


“ምሕ​ረ​ታ​ችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማ​ለ​ዳም እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል ነውና ኤፍ​ሬም ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?


“ዛሬ ቃሉን ብት​ሰሙ እነ​ዚያ እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ ልባ​ች​ሁን አታ​ጽኑ” ብሎ​አ​ልና።


በም​ድረ በዳ በተ​ፈ​ታ​ተ​ኑ​በት ቀን እንደ አሳ​ዘ​ኑት ጊዜ።


ሰዎችም በታላቅ ትኵሳት ተቃጠሉ፤ በነዚህም መቅሠፍቶች ላይ ሥልጣን ያለውን የእግዚአብሔርን ስም ተሳደቡ፤ ክብርንም እንዲሰጡት ንስሓ አልገቡም።


ላሞ​ችም ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ወደ​ሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ አቅ​ን​ተው “እምቧ” እያሉ በጎ​ዳ​ናው ላይ ሄዱ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላ​ሉም፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን አለ​ቆ​ችም እስከ ቤት​ሳ​ሚስ ዳርቻ ድረስ በኋላ በኋላ ይሄዱ ነበር።


እነ​ር​ሱም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ብት​ሰ​ድ​ዱ​አት ስለ አሳ​ዘ​ና​ች​ሁ​አት የበ​ደል መባእ ስጡ እንጂ ባዶ​ዋን አት​ስ​ደ​ዱ​አት፤ የዚ​ያን ጊዜም ትፈ​ወ​ሳ​ላ​ችሁ፤ ስር​የ​ትም ይደ​ረ​ግ​ላ​ች​ኋል፤ አለ​ዚያ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ከእ​ና​ንተ አይ​ር​ቅም” አሉ።


ግብ​ጻ​ው​ያ​ንና ፈር​ዖ​ንም ልባ​ቸ​ውን እን​ዳ​ጸኑ ልባ​ች​ሁን ለምን ታጸ​ና​ላ​ችሁ? በተ​ዘ​ባ​በ​ቱ​ባ​ቸው ጊዜ ያወ​ጡ​አ​ቸው አይ​ደ​ሉ​ምን? እነ​ር​ሱም አል​ሄ​ዱ​ምን?


ወደ​ም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም ተመ​ል​ከቱ፤ በድ​ን​በ​ሩም መን​ገድ ላይ ወደ ቤት​ሳ​ሚስ ብት​ወጣ ይህን እጅግ ክፉ ነገር ያደ​ረ​ገ​ብን እርሱ ነው፤ አለ​ዚ​ያም እን​ዲ​ያው መጥ​ቶ​ብ​ናል እንጂ የመ​ታን የእ​ርሱ እጅ እን​ዳ​ል​ሆነ እና​ው​ቃ​ለን።”


跟着我们:

广告


广告