Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከአ​ንተ፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም፥ ከመ​ን​ደ​ሮ​ች​ህም፥ ከሹ​ሞ​ች​ህም፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም ይሄ​ዳሉ፤ በወ​ን​ዙም ብቻ ይቀ​ራሉ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ጓጕንቸሮቹም ከአንተና ከቤቶችህ፣ ከሹማምትህና ከሕዝብህ ተወግደው በአባይ ወንዝ ብቻ ይወሰናሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ፈርዖንም እረፍት እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ፤ ጌታም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ጓጒንቸሮቹ ከአንተና ከቤትህ ሁሉ፥ ከመኳንንትህና ከሕዝብህም ሁሉ ዘንድ ይወገዳሉ፤ በዐባይ ወንዝ ውስጥ ካልሆነ በቀር፥ በሌላ ቦታ አይገኙም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ጓጕንቸሮቹም ከአንተ፥ ከቤቶችህም፥ ከባርያዎችህም፥ ከሕዝብህም ይሄዳሉ፤ በወንዙም ብቻ ይቀራሉ” አለ።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:11
7 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ግብፅ ተመ​ል​ሰህ ስት​ሄድ በእ​ጅህ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን ተአ​ም​ራ​ቴን ሁሉ በፈ​ር​ዖን ፊት ታደ​ር​ገው ዘንድ ተመ​ል​ከት፤ እኔ ግን ልቡን አጸ​ና​ዋ​ለሁ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አይ​ለ​ቅ​ቅም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ መስ​ማ​ት​ንም እንቢ አለ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ይ​ለ​ቅቅ የፈ​ር​ዖን ልብ ደነ​ደነ።


ሙሴና አሮ​ንም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጡ፤ ሙሴም ፈር​ዖን እንደ ቀጠ​ረው ሰለ ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ መራቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ እንደ አለ አደ​ረገ፤ ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ቹም ከቤት፥ ከመ​ን​ደ​ርም፥ ከሜ​ዳም ሞቱ።


ወን​ዙም ጓጕ​ን​ቸ​ሮ​ችን ያፈ​ላል፤ ወጥ​ተ​ውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አል​ጋ​ህም፥ ወደ ሹሞ​ች​ህም ቤት፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም ላይ፥ ወደ ቡሃ​ቃ​ዎ​ች​ህም፥ ወደ ምድ​ጃ​ዎ​ች​ህም ይገ​ባሉ፤


ሙሴም ፈር​ዖ​ንን፥ “ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ ከአ​ንተ፥ ከሕ​ዝ​ብ​ህም፥ ከቤ​ቶ​ች​ህም እን​ዲ​ጠፉ፥ በወ​ን​ዙም ብቻ እን​ዲ​ቀሩ፥ ለአ​ንተ፥ ለሹ​ሞ​ች​ህም፥ ለሕ​ዝ​ብ​ህም መቼ እን​ድ​ጸ​ልይ ቅጠ​ረኝ” አለው። ፈር​ዖ​ንም፥ “ነገ” አለው።


跟着我们:

广告


广告