Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 6:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እነ​ዚ​ህም እንደ ወገ​ኖ​ቻ​ቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌ​ዊም የሕ​ይ​ወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በትውልዳቸው መሠረት የሌዊ ወንዶች ልጆች ስሞች እነዚህ ነበሩ፤ ጌርሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ናቸው። ሌዊ መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ኖረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 እነዚህ የሌዊ ልጆች ስሞች እንደ ትውልዳቸው ጌርሾን፥ ቀሃት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሌዊ ጌርሾን፥ ቀዓትና መራሪ የተባሉ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነዚህም በየስማቸው የሌዊ ነገድ አባቶች ናቸው፤ ሌዊ በሕይወት የኖረበት ዘመን 137 ዓመት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እነዚህም እንደ ወገኖቻቸው የሌዊ ልጆች ስሞች ጌድሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ ናቸው። የሌዊም የሕይወት ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።

参见章节 复制




ዘፀአት 6:16
22 交叉引用  

የይ​ስ​ሐ​ቅም ዕድሜ መቶ ሰማ​ንያ ዓመት ሆነ።


የሌ​ዊም ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


የሮ​ቤ​ልም ልጆች፤ ሄኖኅ፥ ፍሉስ፥ አስ​ሮን፥ ከርሜ።


ያዕ​ቆ​ብም በግ​ብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀ​መጠ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም መላው የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ።


ዮሴ​ፍም በመቶ ዐሥር ዓመት ዕድ​ሜው ሞተ፤ በሽ​ቱም አሹት፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም በሣ​ጥን ውስጥ አኖ​ሩት።


ዳዊ​ትም እንደ ሌዊ ልጆች እንደ ጌድ​ሶ​ንና እንደ ቀዓት እንደ ሜራ​ሪም በየ​ሰ​ሞ​ና​ቸው መደ​ባ​ቸው።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት ሜራሪ።


የሌዊ ልጆች፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


ሌዋ​ው​ያ​ኑም፥ ከቀ​ዓት ልጆች የአ​ሜ​ሳእ ልጅ መኤ​ትና የዓ​ዛ​ር​ያስ ልጅ ኢዮ​ሔል፥ ከሜ​ራ​ሪም ልጆች የአ​ብዲ ልጅ ቂስና የያ​ሃ​ሌ​ል​ኤል ልጅ ዓዛ​ር​ያስ፥ ከጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች የዛ​ማት ልጅ ዮአ​ክና የዮ​አክ ልጅ ኢዮ​አድ፤


ከሌዊ ወገን እን​በ​ረም የሚ​ባል አንድ ሰው ነበረ፤ እር​ሱም ከሌዊ ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አገባ።


የቀ​ዓ​ትም ልጆች እን​በ​ረም፥ ይስ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ ዑዝ​ኤል ናቸው፤ የቀ​ዓ​ትም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ነው።


እን​በ​ረ​ምም የአ​ባ​ቱን ወን​ድም ልጅ ዮካ​ብ​ድን አገባ፤ አሮ​ን​ንና ሙሴን፥ እኅ​ታ​ቸ​ው​ንም ማር​ያ​ምን ወለ​ደ​ች​ለት፤ የእ​ን​በ​ረ​ምም የሕ​ይ​ወቱ ዘመን መቶ ሠላሳ ሰባት ዓመት ነው።


የሌ​ዊም ልጅ የቀ​ዓት ልጅ የይ​ስ​ዓር ልጅ ቆሬ ከኤ​ል​ያብ ልጆች ከዳ​ታ​ንና ከአ​ቤ​ሮን፥ ከሮ​ቤ​ልም ልጅ ከፋ​ሌት ልጅ ከአ​ው​ናን ጋር ተና​ገረ።


የሌዊ ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው የተ​ቈ​ጠ​ሩት እነ​ዚህ ናቸው፤ ከጌ​ድ​ሶን የጌ​ድ​ሶ​ና​ው​ያን ወገን፥ ከቀ​ዓት የቀ​ዓ​ታ​ው​ያን ወገን፥ ከሜ​ራሪ የሜ​ራ​ራ​ው​ያን ወገን።


የሌዊ ልጆች በየ​ስ​ማ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ጌድ​ሶን፥ ቀዓት፥ ሜራሪ።


የጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ስሞች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እነ​ዚህ ናቸው፤ ሎቤን፥ ሰሜይ።


የቀ​ዓ​ትም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው እን​በ​ረም፥ ይሳ​ዓር፥ ኬብ​ሮን፥ አዛ​ሄል።


የሜ​ራ​ሪም ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ሞሐሊ፥ ሙሲ። የሌ​ዋ​ው​ያን ወገ​ኖች በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እነ​ዚህ ናቸው።


ለጌ​ድ​ሶን የሎ​ቤን ወገን፥ የሰ​ሜ​ይም ወገን ነበ​ሩት፤ የጌ​ድ​ሶን ወገ​ኖች እነ​ዚህ ናቸው።


ለቀ​ዓ​ትም ወገ​ኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋ​ው​ያ​ንም ለነ​በሩ ለካ​ህኑ ለአ​ሮን ልጆች ከይ​ሁዳ ነገድ፥ ከስ​ም​ዖ​ንም ነገድ፥ ከብ​ን​ያ​ምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።


ለጌ​ድ​ሶ​ንም ልጆች ከይ​ሳ​ኮር ነገድ፥ ከአ​ሴ​ርም ነገድ፥ ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምም ነገድ፥ በባ​ሳ​ንም ካለው ከም​ናሴ ነገድ እኩ​ሌታ ዐሥራ ሦስት ከተ​ሞች በዕጣ ተሰ​ጡ​አ​ቸው።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥


跟着我们:

广告


广告