Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 40:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ በው​ስ​ጡም ውኃ ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የመታጠቢያውን ሰን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኑርበት፤ ውሃም አኑርበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የመታጠቢያውን ሳሕን በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኑረህ ውኃ ትጨምርበታለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የመታጠቢያውን ሣሕን በድንኳኑና በመሠዊያው መካከል አስቀምጠህ ውሃ ሙላበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የመታጠቢያውን ሰንም በመገናኛው ድንኳንና በመሠዊያው መካከል አኑረህ ውኃ ትጨምርበታለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 40:7
11 交叉引用  

እነሆ፥ አሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጠ​ላ​ቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደ​ረገ፤ ዞርሁ በድ​ን​ኳ​ኑም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋሁ፥ እል​ልም አል​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ እዘ​ም​ር​ለ​ት​ማ​ለሁ።


የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ከሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ከሴ​ቶች መስ​ተ​ዋት ከናስ አደ​ረገ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ው​ንም መሠ​ዊያ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


በዙ​ሪ​ያ​ውም አደ​ባ​ባ​ዩን ትሠ​ራ​ለህ፤ የአ​ደ​ባ​ባ​ዩ​ንም ደጃፍ መጋ​ረጃ ትዘ​ረ​ጋ​ለህ።


በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ከኃጢአትና ከርኵሰት የሚያነጻ ምንጭ ይከፈታል።


እንደ ምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ፥ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለ ነበረው ሥራ አይደለም፤


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።


跟着我们:

广告


广告