Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 40:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በፊ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ድን​ኳ​ንዋ ተተ​ከ​ለች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እንዲሁም በሁለተኛው ዓመት፣ የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የማደሪያው ድንኳን ተተከለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 እንዲህም ሆነ፤ በሁለተኛው ዓመት በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ማደሪያው ተተከለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ስለዚህ ከግብጽ በወጡ በሁለተኛው ዓመት፥ የመጀመሪያው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን የመገናኛው ድንኳን ተተከለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እንዲህም ሆነ፤ በሁለተኛው ዓመት በፊተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማደሪያው ተተከለ።

参见章节 复制




ዘፀአት 40:17
9 交叉引用  

“ይህ ወር የወ​ሮች መጀ​መ​ሪያ ይሁ​ና​ችሁ፤ የዓ​መ​ቱም መጀ​መ​ሪያ ወር ይሁ​ና​ችሁ።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


ሙሴም ድን​ኳ​ን​ዋን ተከለ፤ እግ​ሮ​ች​ዋ​ንም አኖረ፤ ሳን​ቆ​ች​ዋ​ንም አቆመ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ምሰ​ሶ​ዎ​ች​ዋ​ንም አቆመ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በሃ​ያ​ኛው ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ ደመ​ናው ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ላይ ተነሣ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሙሴ ድን​ኳ​ኑን ፈጽሞ በተ​ከ​ለ​ባት፥ እር​ስ​ዋ​ንና ዕቃ​ዋን ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት፥ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ በቀ​ባና በቀ​ደ​ሰ​ባት ቀን፥


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከግ​ብፅ ምድር በወጡ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በሲና ምድረ በዳ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ድን​ኳ​ን​ዋን በተ​ከ​ሉ​በት ቀን ደመ​ናው የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሸፈ​ናት፤ ከማ​ታም ጀምሮ እስከ ጥዋት ድረስ በድ​ን​ኳኑ ላይ እንደ እሳት ይመ​ስል ነበር።


跟着我们:

广告


广告