Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 4:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ አል​ሁህ፤ አን​ተም ልት​ለ​ቅ​ቃ​ቸው ባት​ፈ​ቅድ፤ እኔ የበ​ኵር ልጅ​ህን እን​ደ​ም​ገ​ድል ዕወቅ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ያመልከኝ ዘንድ ልጄን ልቀቀው” ብዬህ ነበር፤ አንተ ግን እንዳይሄድ ከለከልኸው፤ ስለዚህ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እንዲያገለግለኝ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኩር ልጅህን እገድላለሁ።’”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እኔም ይህ ልጄ እኔን ያመልክ ዘንድ እንድትለቀው ነገርኩህ፤ አንተ ግን እምቢ አልክ፤ ስለዚህ አሁን የአንተን የበኲር ልጅ እገድላለሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ’ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ”’ ትለዋለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 4:23
22 交叉引用  

ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ተገዙ፥ በደ​ልም ሆነ​ባ​ቸው።


ለፀ​ሐይ ቀንን ያስ​ገ​ዛው፤ ምሕ​ረቱ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ነውና፤


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ አሉ​ትም፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔን ማፈ​ርን እስከ መቼ እንቢ ትላ​ለህ? ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን፥ እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በተ​ራ​ራ​ዎ​ችህ ሁሉ ላይ አን​በ​ጣን አመ​ጣ​ለሁ፤


በግ​ብ​ፅም ሀገር ያለ በኵር ሁሉ፥ በዙ​ፋኑ ከሚ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ በወ​ፍጮ እግር እስ​ካ​ለ​ችው እስከ አገ​ል​ጋ​ዪቱ በኵር ድረስ፥ የከ​ብ​ቱም በኵር ሁሉ ይሞ​ታል።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ እኩለ ሌሊት በሆነ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋን ከተ​ቀ​መ​ጠው ከፈ​ር​ዖን በኵር ጀምሮ እስከ ውኃ ቀጅዋ ምር​ኮኛ በኵር ድረስ፥ በግ​ብፅ ምድር በኵ​ሩን ሁሉ፥ የእ​ን​ስ​ሳ​ው​ንም በኵር ሁሉ መታ።


ፈር​ዖ​ንም እኛን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ባለ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰው በኵር ጀምሮ እስከ እን​ስሳ በኵር ድረስ በግ​ብፅ ምድር ያለ​ውን በኵር ሁሉ ገደለ፤ ስለ​ዚህ ወንድ ሆኖ ማሕ​ፀ​ንን የከ​ፈ​ተ​ውን ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሠ​ዋ​ለሁ፤ ነገር ግን የል​ጆ​ችን በኵር ሁሉ እዋ​ጃ​ለሁ።’


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ር​ዖ​ንና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ስለ እስ​ራ​ኤል ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ በመ​ን​ገ​ድም ያገ​ኛ​ቸ​ውን ድካም ሁሉ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ አዳ​ና​ቸው ለአ​ማቱ ነገ​ረው።


እነ​ር​ሱም ቃል​ህን ይሰ​ማሉ፤ አን​ተና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገ​ባ​ላ​ችሁ፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠር​ቶ​ናል፤ አሁ​ንም ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠዋ ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን ትሉ​ታ​ላ​ችሁ።


ከዚ​ህም በኋላ ሙሴና አሮን ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተው እን​ዲህ አሉት፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘በም​ድረ በዳ በዓል ያደ​ር​ግ​ልኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።’ ”


“ግባ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለግ​ብፅ ንጉሥ ለፈ​ር​ዖን ንገ​ረው።”


እን​ዲ​ህም ትለ​ዋ​ለህ፦ ‘የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነ​ሆም፥ እስከ ዛሬ አል​ሰ​ማ​ህም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ግባ፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን በእ​ጅህ ዘርጋ፤ የም​ድ​ሩ​ንም ትቢያ ምታ’ በለው፤ ቅማ​ልም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ በሰ​ውና በእ​ን​ስሳ ላይ ይወ​ጣል።”


አሮ​ንም እጁን ዘረጋ፤ በበ​ት​ሩም የም​ድ​ሩን ትቢያ መታው፤ በሰ​ውና በእ​ን​ስ​ሳም ላይ ቅማል ሆነ፤ በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ የም​ድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቁም፤ እነሆ፥ እርሱ ወደ ውኃ ይወ​ር​ዳል፤ እን​ዲ​ህም በለው፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወደ ፈር​ዖን ገብ​ተህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ያመ​ል​ኩኝ ዘንድ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ማል​ደህ ተነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንም ፊት ቆመህ እን​ዲህ በለው፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ።


ሕዝ​ቤን ልት​ለ​ቃ​ቸው እንቢ ብትል፥ ብት​ይ​ዛ​ቸ​ውም፥


እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤


跟着我们:

广告


广告