Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሌዋ​ዊው ወን​ድ​ምህ አሮን አለ አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ር​ልህ አው​ቃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ እርሱ ሊገ​ና​ኝህ ይመ​ጣል፤ በአ​የ​ህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለ​ዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ፤ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደል? እርሱ ጥሩ እንደሚናገር ዐውቃለሁ፤ እንዲያውም አሁን ወደ አንተ እየመጣ ነው፤ በሚያይህም ጊዜ ከልቡ ደስ ይለዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የጌታም ቁጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ጥሩ እንደሚናገር አውቃለሁ፤ እርሱም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ያይሃልም፤ በልቡም ደስ ይለዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር ሙሴን እጅግ ተቈጥቶ እንዲህ አለው፤ “ሌዋዊ የሆነው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ጥሩ ተናጋሪ መሆኑን ዐውቃለሁ፤ እንዲያውም አሁን ወደ አንተ እየመጣ ነው፤ በሚያይህም ጊዜ ከልብ ደስ ይለዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእግዚአብሔርም ቍጣ በሙሴ ላይ ነደደ እንዲህም አለ፦ “ሌዋዊው ወንድምህ አሮን አለ አይደለምን? እርሱ ደህና እንዲናገር አውቃለሁ፤ እነሆም ደግሞ ሊገናኝህ ይመጣል፤ ባየህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለዋል።

参见章节 复制




ዘፀአት 4:14
19 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያው ቀሠ​ፈው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚ​ያው ሞተ።


ሁለት ጊዜም ከተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ውን መል​ሶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ሎ​ሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ።


ይህም ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመጣ።


እጁ​ንም አነ​ሣ​ባ​ቸው። በም​ድረ በዳ ይጥ​ላ​ቸው ዘንድ፥


ሙሴም፥ “ጌታ ሆይ፥ እማ​ል​ድ​ሃ​ለሁ፤ መና​ገር የሚ​ችል የም​ት​ል​ከው ሌላ ሰው ፈልግ” አለው።


ይህ​ች​ንም ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን አለው፥ “ሄደህ በም​ድረ በዳ ሙሴን ተገ​ና​ኘው፤” ሄዶም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራራ ተገ​ና​ኘው፤ እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም ተሳ​ሳሙ።


እነ​ር​ሱም፥ “በውኑ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሙሴ ብቻ ተና​ግ​ሮ​አ​ልን? በእ​ኛስ ደግሞ የተ​ና​ገረ አይ​ደ​ለ​ምን?” አሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማ።


ሥር​ዐት እን​ዳ​ና​ከ​ብድ ሌላም ሸክም እን​ዳ​ን​ጨ​ምር መን​ፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እና​ዝ​ዛ​ች​ኋ​ለን።


ወን​ድ​ሜን ቲቶን ስላ​ላ​ገ​ኘ​ሁት ለሰ​ው​ነቴ ዕረ​ፍት አላ​ገ​ኘ​ሁም፤ ነገር ግን ከእ​ርሱ ተለ​ይች ወደ መቄ​ዶ​ንያ ሄድሁ።


የክ​ር​ስ​ቶ​ስን ያይ​ደለ፥ ሁሉም የራ​ሱን ጉዳይ ያስ​ባ​ልና።


ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ላክሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ቀሠ​ፍ​ኋ​ቸው፤


ያዕ​ቆ​ብና ልጆቹ ወደ ግብጽ በገቡ ጊዜ ግብ​ጻ​ው​ያን አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን ላከ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ከግ​ብጽ አው​ጥ​ተው በዚህ ቦታ አኖ​ሩ​አ​ቸው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰው ወደ ዔሊ መጥቶ እን​ዲህ አለው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ በግ​ብፅ በፈ​ር​ዖን ቤት ባሪ​ያ​ዎች ሳሉ ለአ​ባ​ትህ ቤት ተገ​ለ​ጥሁ፤


跟着我们:

广告


广告