Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 37:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 መቅ​ረ​ዝ​ዋ​ንም ከጥሩ ወርቅ አደ​ረገ፤ መቅ​ረ​ዝ​ዋ​ንም ከእ​ግ​ር​ዋና ከአ​ገ​ዳዋ ጋር በተ​ቀ​ረጸ ሥራ አደ​ረገ፤ ጽዋ​ዎ​ች​ዋን፥ ጕብ​ጕ​ቦ​ች​ዋን፥ አበ​ቦ​ች​ዋን ከዚ​ያው በአ​ን​ድ​ነት አደ​ረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠሩት፤ መቆሚያውንና ዘንጉን ቀጥቅጠው አበጁት፤ የአበባ ቅርጽ ያላቸው ጽዋዎች፣ እንቡጦችና የፈኩ አበቦች ከርሱ ጋራ አንድ ወጥ ሆነው ተሠርተው ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 መቅረዙን ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 መቅረዙንም ከንጹሕ ወርቅ ሠራ፤ ማቆሚያውንና ዘንጉንም ከተቀጠቀጠ ወርቅ አበጀ፤ ለጌጥ የሚሆኑትንም የአበባዎች ቅርጽ ከነእንቡጣቸውና ከነቀንበጣቸው አንድ ወጥ አድርጎ ሠራቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 መቅረዙንም ከጥሩ ወርቅ አደረገ፤ መቅረዙንም ከእግሩና ከአገዳው ጋር በተቀረጸ ሥራ አደረገ፤ ጽዋዎቹን፥ ጉብጉቦቹን፥ አበቦቹን ከዚያው በአንድነት አደረገ።

参见章节 复制




ዘፀአት 37:17
17 交叉引用  

ለወ​ር​ቁም መቅ​ረ​ዞ​ችና ለቀ​ን​ዲ​ሎ​ችም ወር​ቁን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤ ለብ​ሩም መቅ​ረ​ዞች እንደ መቅ​ረዙ ሁሉ ሥራ ብሩን በየ​መ​ቅ​ረ​ዙና በየ​ቀ​ን​ዲሉ በሚ​ዛን ሰጠው፤


በየ​ጥ​ዋ​ቱና በየ​ማ​ታ​ውም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ጣፋ​ጩን ዕጣን ያሳ​ር​ጋሉ፤ የገ​ጹ​ንም ኅብ​ስት በን​ጹሕ ገበታ ላይ፥ የወ​ር​ቁን መቅ​ረ​ዝና ቀን​ዲ​ሎ​ቹ​ንም ማታ ማታ እን​ዲ​ያ​በሩ ያዘ​ጋ​ጃሉ፤ እኛም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ እን​ጠ​ብ​ቃ​ለን፤ እና​ንተ ግን ትታ​ች​ሁ​ታል።


የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውን፥ ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም፥ ከዕ​ቃው ሁሉ የነ​ጻ​ውን መቅ​ረዝ፥


ለማ​ፍ​ሰ​ሻም ይሆኑ ዘንድ በገ​በ​ታው ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ዕቃ​ዎች፥ ወጭ​ቶ​ቹ​ንና ጭል​ፋ​ዎ​ቹን፥ ጽዋ​ዎ​ቹ​ንም፥ መቅ​ጃ​ዎ​ቹ​ንም ከጥሩ ወርቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው።


በስ​ተ​ጎ​ንዋ ስድ​ስት ቅር​ን​ጫ​ፎች ወጡ​ላት፤ ሦስቱ የመ​ቅ​ረ​ዝዋ ቅር​ን​ጫ​ፎች በአ​ንድ ወገን፥ ሦስ​ቱም የመ​ቅ​ረ​ዝዋ ቅር​ን​ጫ​ፎች በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን ወጡ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጥሩ መቅ​ረዝ ላይ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሁል ጊዜ እስ​ኪ​ነጋ አብ​ሩ​አ​ቸው።


እኔም መልሼ፦ በመቅረዙ በስተ ቀኝና በስተ ግራ ያሉ እነዚህ ሁለት የወይራ ዛፎች ምንድር ናቸው? አልሁት።


እርሱም፦ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦እነሆ፥ ሁለንተናው ወርቅ የሆነውን መቅረዝ አየሁ፣ የዘይትም ማሰሮ በራሱ ላይ ነበረ፥ ሰባትም መብራቶች ነበሩበት፣ በራሱም ላይ ለነበሩት መብራቶች ሰባት ቧንቧዎች ነበሩአቸው።


የመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ሥራዋ እን​ዲህ ነበረ። ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ወርቅ የሆነ አፅ​ቆ​ችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበ​ቦ​ች​ዋም ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ሳ​የው ምሳሌ መቅ​ረ​ዝ​ዋን እን​ዲሁ አደ​ረገ።


መብራትንም አብርተው ከዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያኖሩታል፤በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ዪ​ቱም ድን​ኳን ተዘ​ጋ​ጅታ ነበ​ርና፥ በእ​ር​ስ​ዋም ቅድ​ስት በም​ት​ባ​ለው ውስጥ መቅ​ረ​ዙና ጠረ​ጴ​ዛው፥ የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱም ኅብ​ስት ነበ​ረ​ባት።


የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፤


跟着我们:

广告


广告