Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 36:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነ​በ​ሩት በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ሁሉ ድን​ኳ​ኑን ከዐ​ሥር መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሠሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ሠሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በጥ​ልፍ ሥራ ኪሩ​ቤ​ልን አደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሥራ ችሎታ ካላቸው ሰዎች መካከል ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ሁሉ የማደሪያውን ድንኳን በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ በጥልፍ ዐዋቂ፣ ኪሩቤል ከተጠለፉበት ከዐሥር መጋረጃዎች ሠሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሥራ ሲሠሩ ከነበሩት ጥበበኞች የሆኑት ሁሉ ማደሪያውን ሠሩ፤ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ፥ ኪሩቤልም የተጠለፈባቸው ዐሥር መጋረጃዎች ሠሩ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ሥራውን ከሚያከናውኑት መካከል እጅግ ጥበበኞች የነበሩት የተቀደሰውን ድንኳን ሠሩ፤ እነርሱም ድንኳኑን ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተሉ፥ የኪሩቤል ሥዕል ከተጠለፈባቸው ዐሥር የበፍታ መጋረጃዎች ሠሩት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በእነርሱም ዘንድ ያሉት ሥራ ሲሠሩ የነበሩት በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ ማደሪያውን ከአሥር መጋረጆች ሠሩ፤ እነርሱንም ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ሠሩ፤ በእነርሱም ላይ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን አደረጉባቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 36:8
14 交叉引用  

በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ኑም ውስጥ ቁመ​ታ​ቸው ዐሥር ክንድ የሆነ ከወ​ይራ እን​ጨት ሁለት ኪሩ​ቤ​ልን ሠራ።


ዳዊ​ትም በከ​ተ​ማው ለራሱ ቤቶ​ችን ሠራ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ስፍራ አዘ​ጋጀ፤ ድን​ኳ​ንም ተከ​ለ​ላት።


ሰሎ​ሞ​ንም ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ስ​ራ​ኤል ጉባኤ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪያ ሙሴ በም​ድረ በዳ የሠ​ራው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ስ​ክር ድን​ኳን በዚያ ነበ​ረና በገ​ባ​ዖን ወዳ​ለው የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ሄዱ።


በቅ​ድ​ስተ ቅዱ​ሳ​ንም ውስጥ ከእ​ን​ጨት ሥራ ሁለ​ቱን ኪሩ​ቤል ሠራ፤ በወ​ር​ቅም ለበ​ጣ​ቸው።


ሁለት ኪሩ​ቤል ከተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ በሁ​ለት ወገን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።


በዚ​ያም እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ፥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁ​ለት ኪሩ​ቤል መካ​ከል፥ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ ሆኜ እነ​ጋ​ገ​ር​ሃ​ለሁ።


እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚ​ሆን የአ​ሂ​ሳ​ሚ​ክን ልጅ ኤል​ያ​ብን ሰጠሁ፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ዕው​ቅ​ትን ሰጠሁ።


የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን፥ የቃል ኪዳ​ኑ​ንም ታቦት፥ በእ​ር​ሱም ላይ ያለ​ውን የስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውን፥ የድ​ን​ኳ​ኑ​ንም ዕቃ ሁሉ፤


“በእ​ና​ንተ ዘንድ ያለ፥ በልቡ ጥበ​በኛ የሆነ ሁሉ መጥቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ ያድ​ርግ።


የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መጋ​ረጃ ርዝ​መት ሃያ ስም​ንት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ ነበረ፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ሁሉ ልክ ትክ​ክል ነበረ።


ወር​ቁ​ንም ቀጥ​ቅ​ጠው እንደ ቅጠል ስስ አደ​ረ​ጉት፤ እንደ ፈት​ልም ቈረ​ጡት። ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ ሰማ​ያዊ፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተ​ለም ጥሩ በፍታ፥ ከእ​ርሱ ጠለፉ።


跟着我们:

广告


广告