Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 35:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሴቶ​ችም በእ​ጃ​ቸው ፈተሉ፤ የፈ​ተ​ሉ​ት​ንም ሰማ​ያ​ዊ​ውን፥ ሐም​ራ​ዊ​ው​ንም፥ ቀዩ​ንም ግምጃ፥ ጥሩ​ው​ንም በፍታ አመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ጥበበኞች የሆኑ ሴቶች ሁሉ በእጃቸው ፈተሉ፤ የፈተሉትንም ሰማያዊ ሐምራዊ ወይም ቀይ ማግ ወይም ቀጭን በፍታ አመጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶች ሁሉ በእጃቸው ፈተሉ፥ የፈተሉትንም ሰማያዊውን፥ ሐምራዊውን፥ ቀይ ግምጃውንና ጥሩውን በፍታ አመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 የእጅ ጥበብ ችሎታ ያላቸው ሴቶችም በእጃቸው የሠሩትን ጥሩ በፍታና ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ከፈይ ይዘው መጡ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በልባቸው ጥበበኞች የሆኑ ሴቶችም በእጃቸው ፈተሉ፥ የፈተሉትንም ሰማያዊውን ሐምራዊውንም ቀዩንም ግምጃ፥ ጥሩውንም በፍታ አመጡ።

参见章节 复制




ዘፀአት 35:25
16 交叉引用  

ሴቶ​ቹም ለማ​ም​ለ​ኪያ ዐፀድ መጋ​ረጃ ይፈ​ት​ሉ​ባ​ቸው የነ​በ​ሩ​ትን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ውስጥ ያሉ​ትን የሰ​ዶ​ማ​ው​ያ​ንን ቤቶች አፈ​ረሰ።


እነ​ሆም፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ሁሉ የሚ​ሆኑ የካ​ህ​ና​ትና የሌ​ዋ​ው​ያን ክፍ​ሎች በዚህ አሉ፤ ለሁ​ሉም ዓይ​ነት አገ​ል​ግ​ሎ​ትና ሥራ በጥ​በ​ብና በነ​ፍሱ ፈቃድ የሚ​ሠራ ሁሉ ከአ​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈጽ​መው ይታ​ዘ​ዙ​ሃል” አለው።


አን​ተም የጥ​በብ መን​ፈስ ለሞ​ላ​ሁ​ባ​ቸው፥ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ተና​ገር። እነ​ር​ሱም ካህን ሆኖ እን​ዲ​ያ​ገ​ለ​ግ​ለኝ ለአ​ሮን ለቤተ መቅ​ደስ የሚ​ሆን የተ​ለየ ልብስ ይሥሩ፤


እኔም እነሆ፥ ከዳን ነገድ የሚ​ሆን የአ​ሂ​ሳ​ሚ​ክን ልጅ ኤል​ያ​ብን ሰጠሁ፤ ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ለሆ​ኑት ሁሉ ዕው​ቅ​ትን ሰጠሁ።


ስዕ​ለት የተ​ሳለ ሁሉ፥ የብ​ር​ንም፥ የና​ስ​ንም ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን አቀ​ረበ፤ የማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ያለው ሁሉ ለድ​ን​ኳኑ ማገ​ል​ገያ ለሚ​ያ​ስ​ፈ​ል​ገው ሥራ አመጣ።


ልባ​ቸ​ውም በጥ​በብ ያስ​ነ​ሣ​ቸው ሴቶች ሁሉ የፍ​የ​ልን ጠጕር ፈተሉ።


“ባስ​ል​ኤ​ልና ኤል​ያብ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም ማገ​ል​ገያ ሥራ ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን የሰ​ጣ​ቸው በል​ባ​ቸ​ውም ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ረጉ።”


ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።


ጴጥ​ሮ​ስም ተነ​ሥቶ አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ በደ​ረ​ሰም ጊዜ ወደ ሰገ​ነት አወ​ጡት፤ ባል​ቴ​ቶ​ችም ሁሉ ወደ እርሱ መጥ​ተው በፊቱ ቆሙ፤ ያለ​ቅ​ሱ​ላ​ትም ነበር፤ ዶር​ቃ​ስም በሕ​ይ​ወት ሳለች የሠ​ራ​ች​ውን ቀሚ​ሱ​ንና መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ውን አሳ​ዩት።


በጌ​ታ​ችን ስም መከራ የተ​ቀ​በ​ሉ​ትን የጢ​ሮ​ፊ​ሞ​ና​ንና የጢ​ሮ​ፊ​ሞ​ስን ወገ​ኖች ሰላም በሉ። በጌ​ታ​ችን ስም ብዙ የደ​ከ​መች እኅ​ታ​ች​ንን ጠር​ሴ​ዳን ሰላም በሉ።


ለእ​ና​ንተ ብዙ የደ​ከ​መ​ች​ላ​ች​ሁን ማር​ያ​ም​ንም ሰላም በሉ።


በዚ​ህም አይ​ሁ​ዳዊ፥ ወይም አረ​ማዊ የለም፤ ገዢ፥ ወይም ተገዢ የለም፤ ወንድ፥ ወይም ሴት የለም፤ ሁላ​ችሁ በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አንድ ናች​ሁና።


ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና።


跟着我们:

广告


广告