Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 35:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ወን​ዶ​ችና ሴቶ​ችም ልባ​ቸው እንደ ፈቀደ ማር​ዳ​ዎ​ችን፥ ሎቲ​ዎ​ች​ንም፥ ቀለ​በ​ቶ​ች​ንም፥ ድሪ​ዎ​ች​ንም፥ የወ​ርቅ ጌጦ​ች​ንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎ​ችም ሁሉ የወ​ርቅ ስጦታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቀ​ረቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ፈቃደኛ የነበሩ ሁሉ፣ ወንዶችም ሴቶችም መጥተው ከሁሉም ዐይነት የወርቅ ጌጦች አመጡ፤ የአፍንጫ ጌጦችን፣ ሎቲዎችን፣ ቀለበቶችን፣ ድሪዎችንና ጌጣጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሁሉም ወርቃቸውን እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ልባቸው የተነሣሣ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ የአፍንጫ ጌጦችን፥ ሎቲዎችን፥ ቀለበቶችን፥ ድሪዎችን፥ የወርቅ ጌጦችን ሁሉ አመጡ፤ ሰዎች ሁሉ የወርቅ ስጦታ ለጌታ አመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ስጦታ ማቅረብ የፈለገ ሴቱም ወንዱም እያንዳንዱ የደረት ጌጥ፥ የጆሮ ወርቅ፥ የጣት ቀለበት፥ ድሪዎችና የወርቅ ጌጦችን አምጥቶ ለእግዚአብሔር የተለዩ እንዲሆኑ አደረገ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ወንዶችና ሴቶችም ልባቸው እንደ ፈቀደ ማርዳዎችን፥ ሎቲዎችንም፥ ቀለበቶችንም፥ ድሪዎችንም፥ የወርቅ ጌጦችንም ሁሉ አመጡ፤ ሰዎችም ሁሉ የወርቅ ስጦታ ወደ እግዚአብሔር አቀረቡ።

参见章节 复制




ዘፀአት 35:22
18 交叉引用  

ኢዮ​አ​ስም ካህ​ና​ቱን፥ “ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ገ​ባ​ውን የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ገን​ዘብ ሁሉ፥ ስለ ነፍ​ሱም ዋጋ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን ገን​ዘብ፥ በል​ባ​ቸ​ውም ፈቃድ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት የሚ​ያ​መ​ጡ​ትን ገን​ዘብ ሁሉና፥


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “አሁን እጃ​ች​ሁን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አን​ጽ​ታ​ችሁ ቅረቡ፤ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና የም​ስ​ጋ​ና​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጡ” ብሎ ተና​ገረ። ጉባ​ኤ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና የም​ስ​ጋ​ና​ውን መሥ​ዋ​ዕት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አመጡ፤ ልባ​ቸ​ውም የፈ​ቀደ ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አመጡ።


አሮ​ንም፥ “በሚ​ስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና በሴ​ቶች ልጆ​ቻ​ችሁ ጆሮ ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች አም​ጡ​ልኝ” አላ​ቸው።


ሕዝ​ቡም ሁሉ በጆ​ሮ​ዎ​ቻ​ቸው ያሉ​ትን የወ​ርቅ ጌጦች ወደ አሮን አመ​ጡ​ለት።


ከእ​ነ​ር​ሱም ሰው ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ልቡ እን​ዳ​ነ​ሣ​ሣው፥ መን​ፈ​ሱም እሺ እን​ዳ​ሰ​ኘው ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ለማ​ገ​ል​ገ​ያ​ውም ሁሉ ለመ​ቅ​ደስ ልብስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስጦታ አመጡ።


ሰማ​ያ​ዊም፥ ሐም​ራ​ዊም፥ ቀይ ግም​ጃም፥ የተ​ፈ​ተለ በፍ​ታም፥ የፍ​የል ጠጕ​ርም፥ ቀይ የአ​ውራ በግ ቍር​በ​ትም፥ የአ​ቆ​ስጣ ቍር​በ​ትም ያላ​ቸው ሰዎች ሁሉ አመጡ።


የጆሮ እን​ጥ​ል​ጥ​ሉ​ንም፥ አን​ባ​ሩ​ንም፥ መሸ​ፈ​ኛ​ው​ንም፥ ቀጸ​ላ​ው​ንም፥


የመ​ቅ​ደ​ሴ​ንም ስፍራ ያከ​ብሩ ዘንድ የሊ​ባ​ኖስ ክብር፥ ጥዱና አስ​ታው፥ ባር​ሰ​ነ​ቱም ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፥


ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ የተ​ር​ሴ​ስም መር​ከ​ቦች አስ​ቀ​ድ​መው ይመ​ጣሉ፤ ልጆ​ችሽ ስለ ከበ​ረው ስለ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወር​ቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ።


በጌ​ጥም አስ​ጌ​ጥ​ሁሽ፤ በእ​ጅ​ሽም ላይ አን​ባር፥ በአ​ን​ገ​ት​ሽም ላይ ድሪ አደ​ረ​ግ​ሁ​ልሽ።


ሰውም ሁሉ ከአ​ገ​ኘው ከወ​ርቅ ዕቃ፥ ከእ​ግር አል​ቦም፥ ከአ​ም​ባ​ርም፥ ከቀ​ለ​በ​ትም ከጕ​ት​ቻም፥ ከድ​ሪ​ውም ስለ እኛ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታስ​ተ​ሰ​ር​ዩ​ልን ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አም​ጥ​ተ​ናል” አሉት።


ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት።


跟着我们:

广告


广告