Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 34:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 አሕ​ዛ​ብን ከፊ​ትህ በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ ሀገ​ር​ህን አሰ​ፋ​ለሁ፤ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊትም ለመ​ታ​የት በዓ​መት ሦስት ጊዜ ስት​ወጣ ማንም ምድ​ር​ህን አይ​መ​ኝም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 አሕዛብን ከፊትህ አስወጣለሁ፤ ድንበርህን አሰፋለሁ፤ በዓመት ሦስት ጊዜ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ለመቅረብ ስትወጣ፣ ምድርህን ማንም አይመኝም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 አሕዛብን ከፊትህ አስወግዳለሁ፥ ድንበርህንም አሰፋለሁ፤ በጌታ አምላክህ ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 አሕዛብን ሁሉ አስወግጄ ግዛታችሁን አሰፋለሁ፤ ስለዚህ በእነዚህ በሦስት በዓላት ወቅት ወደ እኔ ስትቀርቡ አገራችሁን ለመውረር የሚመኝ ማንም አይመጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 አሕዛብን ከፊትህ አወጣለሁ፥ አገርህንም አሰፋለሁ፤ በአምላክህም በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት በዓመት ሦስት ጊዜ ስትወጣ ማንም ምድርህን አይመኝም።

参见章节 复制




ዘፀአት 34:24
19 交叉引用  

በዚ​ያ​ችም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ብ​ራም ተስፋ ያደ​ረ​ገ​ለ​ትን ቃል ኪዳን አጸና፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “ከግ​ብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ ኤፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ድረስ ይህ​ችን ምድር ለዘ​ርህ እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤


እስ​ራ​ኤ​ልም ከሴ​ቄም ሄደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መፍ​ራት በዙ​ሪ​ያ​ቸው ባሉት ከተ​ሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ለማ​ሳ​ደድ አል​ተ​ከ​ተ​ሉ​አ​ቸ​ውም።


የጢ​ሮስ ንጉሥ ኪራም ለአ​ባቱ ለዳ​ዊት በዘ​መኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎ​ሞን በአ​ባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመ​ሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን ወደ ሰሎ​ሞን ላከ።


ያግ​ቤ​ጽም፥ “እባ​ክህ፥ መባ​ረ​ክን ባር​ከኝ፥ ሀገ​ሬ​ንም አስ​ፋው፤ እጅ​ህም ከእኔ ጋር ትሁን፤ እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ነ​ኝም ምል​ክት አድ​ር​ግ​ልኝ” ብሎ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን አም​ላክ ጠራ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የለ​መ​ነ​ውን ሰጠው።


በይ​ሁ​ዳም ዙሪያ በነ​በሩ የም​ድር መን​ግ​ሥ​ታት ሁሉ ላይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ድን​ጋጤ ሆነ፤ ከኢ​ዮ​ሳ​ፍ​ጥም ጋር አል​ተ​ዋ​ጉም።


አንተ ቤቱን በው​ስ​ጥም በው​ጭም፥ በዙ​ሪ​ያው ያለ​ው​ንም ሁሉ አል​ሞ​ላ​ህ​ለ​ት​ምን? የእ​ጁ​ንም ሥራ ባር​ከ​ህ​ለ​ታል፥ ከብ​ቱ​ንም በም​ድር ላይ አብ​ዝ​ተ​ህ​ለ​ታል።


ዐይ​ኖቼን ወደ ተራ​ሮች አነ​ሣሁ፤ ረድ​ኤቴ ከወ​ዴት ይምጣ?


ሕዝቤ ሆይ፥ ስማኝ እነ​ግ​ር​ሃ​ለ​ሁም፤ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እመ​ሰ​ክ​ር​ል​ሃ​ለሁ።


መል​አ​ኬ​ንም ከአ​ንተ ጋር በፊ​ትህ እል​ካ​ለሁ፤ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ውን፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ያወ​ጣ​ቸ​ዋል።


በዚህ ቀን የማ​ዝ​ዝ​ህን ነገር ጠብቅ፤ እነሆ፥ እኔ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ከፊ​ትህ አወ​ጣ​ለሁ።


ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


“ከፊ​ታ​ችሁ የማ​ሳ​ድ​ዳ​ቸው አሕ​ዛብ በእ​ነ​ዚህ ሁሉ ረክ​ሰ​ዋ​ልና በእ​ነ​ዚህ ነገ​ሮች ሁሉ አት​ር​ከሱ።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና ማንም ሊጐ​ዳህ የሚ​ነ​ሣ​ብህ የለም፤ በዚች ከተማ ብዙ ሕዝብ አሉ​ኝና።”


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ነገ​ረህ ድን​በ​ር​ህን ባሰ​ፋ​ልህ ጊዜ፥ ሰው​ነ​ት​ህም ሥጋ መብ​ላት ስለ ወደ​ደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ ሰው​ነ​ትህ ከወ​ደ​ደ​ችው ሁሉ ብላ።


በዓ​መት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰ​ባቱ ሱባ​ዔም በዓል፥ በዳ​ስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ይታይ፤


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ባ​ቶ​ችህ እንደ ማለ​ላ​ቸው ዳር​ቻ​ህን ቢያ​ሰፋ፥ ለአ​ባ​ቶ​ችህ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ ብሎ የተ​ና​ገ​ረ​ውን ምድር ሁሉ ቢሰ​ጥህ፥


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ወ​ር​ሳት ወደ​ም​ት​ገ​ባ​ባት ምድር ባመ​ጣህ ጊዜ፥ ከፊ​ት​ህም ብዙና ታላ​ላቅ አሕ​ዛ​ብን፥ ከአ​ንተ የበ​ለ​ጡ​ትን፥ የበ​ረ​ቱ​ት​ንም ሰባ​ቱን አሕ​ዛብ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊ​ውን፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ው​ንም ባወጣ ጊዜ፥


跟着我们:

广告


广告