ዘፀአት 32:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)29 ሙሴም፥ “ዛሬ በረከትን እንዲያወርድላችሁ ከእናንተ እያንዳንዱ ከልጁና፥ ከወንድሙ የተነሣ እግዚአብሔርን በእጃችሁ ደስ አሰኛችሁት” አላቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም29 ከዚያም ሙሴ፣ “በራሳችሁ ወንዶች ልጆችና ወንድሞች ላይ በመነሣታችሁ፣ በዛሬዋ ቀን ለእግዚአብሔር የተለያችሁ ሆናችኋል፤ በዛሬዋም ዕለት ባርኳችኋል” አለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)29 ሙሴም “ዛሬ በላያችሁ ላይ በረከት እንዲያወርድ እያንዳንዱ በልጁና በወንድሙ ላይ ተነሥቷልና ዛሬ ለጌታ እጃችሁን ቀደሳችሁ” አለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም29 ሙሴም ሌዋውያንን እንዲህ አለ፤ “ዛሬ ልጆቻችሁንና ወንድሞቻችሁን በመግደል እግዚአብሔርን የምታገለግሉ ካህናት ሆናችሁ ራሳችሁን ቀድሳችኋል፤ እግዚአብሔርም በረከቱን ሰጥቶአችኋል።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)29 ሙሴም፦ ዛሬ በረከትን እንዲያወርድላችሁ እያንዳንዳችሁ በልጃችሁና በወንድማችሁ ላይ ዛሬ እጃችሁን ለእግዚአብሔር ቅዱስ አድርጉ አለ። 参见章节 |