Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 32:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሙሴም አሮ​ንን፥ “ይህን ታላቅ ኀጢ​አት ታመ​ጣ​በት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደ​ረ​ገህ?” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሙሴም አሮንን፣ “ወደዚህ አስከፊ ኀጢአት ትመራቸው ዘንድ እነዚህ ሕዝብ ምን አደረጉህ?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሙሴም አሮንን፦ “ይህንን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ?” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 አሮንንም “ከቶ ይህ ሕዝብ ምን አድርጎህ ነው ይህን የመሰለ አስከፊ ኃጢአት እንዲሠራ ያደረግኸው?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሙሴም አሮንን፦ ይህን ታላቅ ኃጢአት ታመጣበት ዘንድ ይህ ሕዝብ ምን አደረገህ? አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 32:21
11 交叉引用  

አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን ጠርቶ አለው፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምንስ ክፉ ሠራ​ሁ​ብህ? በእ​ኔና በመ​ን​ግ​ሥቴ ላይ ትልቅ ኀጢ​አት አው​ር​ደ​ሃ​ልና፤ ማንም የማ​ያ​ደ​ር​ገው የማ​ይ​ገባ ሥራ በእኔ ሠራ​ህ​ብኝ።”


አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ከሕ​ዝቡ አንዱ ባለ​ማ​ወቅ ከሚ​ስ​ትህ ጋር ሊተኛ ጥቂት በቀ​ረው ነበር፤ ኀጢ​አ​ት​ንም ልታ​መ​ጣ​ብን ነበር።”


ስለ በደ​ለ​ውና እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ስላ​ሳ​ተ​በት ስለ ኢዮ​ር​ብ​ዓም ኀጢ​አት እስ​ራ​ኤ​ልን ይጥ​ላል።”


አንድ ነቢ​ይም ወደ እስ​ራ​ኤል ንጉሥ መጥቶ፥ “የሶ​ርያ ንጉሥ ወልደ አዴር በሚ​መ​ጣው ዓመት ይመ​ጣ​ብ​ሃ​ልና፥ በርታ፤ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ው​ንም ዕወቅ” አለው።


የሠ​ሩ​ት​ንም ጥጃ ወስዶ በእ​ሳት አቀ​ለ​ጠው፤ ፈጨው፤ አደ​ቀ​ቀ​ውም፤ በው​ኃም ላይ በተ​ነው፤ ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች አጠ​ጣ​ቸው።


አሮ​ንም እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእኔ ላይ አት​ቈጣ፤ የዚ​ህን ሕዝብ ጠባይ አንተ ታው​ቃ​ለህ።


ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ይህ በጆ​ሮዬ የም​ሰ​ማው የበ​ጎች ጩኸ​ትና የበ​ሬ​ዎች ግሣት ምን​ድር ነው?” አለ።


አሁ​ንም ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! የእ​ኔን የአ​ገ​ል​ጋ​ይ​ህን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእኔ ላይ አስ​ነ​ሥ​ቶህ እን​ደ​ሆነ፥ ቍር​ባ​ን​ህን ይቀ​በል፤ የሰው ልጆች ግን ቢሆኑ፦ ሂድ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት አም​ልክ ብለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ላይ እን​ዳ​ል​ቀ​መጥ ዛሬ ጥለ​ው​ኛ​ልና በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ርጉ​ማን ይሁኑ።


跟着我们:

广告


广告