Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 32:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አሁ​ንም ተቈ​ጥቼ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ለታ​ላቅ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 አሁንም በእነርሱ ላይ፣ ቍጣዬ እንዲነድድና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ ከዚያም አንተን ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 አሁንም ቁጣዬ በእነርሱ ላይ እንዲነድና እንዳጠፋቸው ተወኝ፤ ከአንተም ታላቅ ሕዝብ አደርጋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አሁንም እነሆ፥ በእነርሱ ላይ እጅግ ተቈጥቼ ላጠፋቸው ስለ ተዘጋጀሁ ተወኝ፤ አንተንም ታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 አሁንም ቁጣዬ እንዲቃጠልባቸው እንዳጠፋቸውም ተወኝ፤ አንተንም ለታላቅ ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 32:10
21 交叉引用  

ታላቅ ሕዝ​ብም አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ እባ​ር​ክ​ሃ​ለሁ፤ ስም​ህ​ንም ከፍ ከፍ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ቡሩ​ክም ትሆ​ና​ለህ፤ የሚ​ባ​ር​ኩ​ህ​ንም እባ​ር​ካ​ለሁ፤


በመ​ር​ከ​ቦች ወደ ባሕር የሚ​ወ​ርዱ፥ በብዙ ውኃ ሥራ​ቸ​ውን የሚ​ሠሩ፥


ቍጣ​ዬም ይጸ​ና​ባ​ች​ኋል፤ በሰ​ይ​ፍም አስ​ገ​ድ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁም መበ​ለ​ቶች፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ድሀ-አደ​ጎች ይሆ​ናሉ።


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ም​ላኩ ፊት ጸለየ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ በታ​ላቅ ኀይ​ልና በጽኑ እጅ ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ኸው በሕ​ዝ​ብህ ላይ ለምን ተቈ​ጣህ?


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ሰፈሩ ሲቀ​ርብ ጥጃ​ው​ንም ዘፈ​ኑ​ንም አየ፤ የሙ​ሴም ቍጣ ተቃ​ጠለ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም ሁለ​ቱን ጽላት ከእጁ ጥሎ ከተ​ራ​ራው በታች ሰበ​ራ​ቸው።


ወተ​ትና ማርም ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ምድር አስ​ገ​ባ​ሃ​ለሁ፤ አን​ገተ ደን​ዳና ስለ​ሆኑ ሕዝ​ብህ በመ​ን​ገድ ላይ እን​ዳ​ላ​ጠ​ፋህ እኔ ከአ​ንተ ጋር አል​ወ​ጣም።”


አን​ተም ስለ​ዚህ ሕዝብ አት​ጸ​ልይ፤ በመ​ከ​ራ​ቸው ቀን ወደ እኔ በጮኹ ጊዜ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምና ስለ እነ​ርሱ አት​ጸ​ልይ፤ በም​ል​ጃና በጸ​ሎት አት​ማ​ልድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ለዚህ ሕዝብ ስለ መል​ካም አት​ጸ​ል​ይ​ላ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አለኝ፥ “ሙሴና ሳሙ​ኤል በፊቴ ቢቆ​ሙም፥ ልቤ ወደ​ዚህ ሕዝብ አያ​ዘ​ነ​ብ​ልም፤ እነ​ዚ​ህን ሕዝ​ቦች ከፊቴ አባ​ር​ራ​ቸው፤ ይውጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፥ “ስለ​ዚህ ሕዝብ አንተ አት​ጸ​ልይ፤ ይቅር እላ​ቸው ዘንድ አት​ማ​ል​ደኝ፤ የእ​ነ​ር​ሱን ነገር አል​ሰ​ማ​ህ​ምና ትለ​ም​ን​ላ​ቸው ዘንድ ወደ እኔ አት​ምጣ።”


ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት በም​ድረ በዳ በት​እ​ዛዜ ሂዱ አል​ኋ​ቸው፤ አል​ሄ​ዱ​ምም፤ ሰው ቢያ​ደ​ር​ገው ኖሮ በሕ​ይ​ወት የሚ​ኖ​ር​በ​ት​ንም ሕጌን አፈ​ረሱ፤ ሰን​በ​ታ​ቴ​ንም ፈጽ​መው አረ​ከሱ። በዚ​ህም ጊዜ አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ቍጣ​ዬን በም​ድረ በዳ አፈ​ስ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ አልሁ።


በሞት እቀ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም፤ አን​ተ​ንና የአ​ባ​ት​ህን ቤት ግን ለታ​ላ​ቅና ከዚህ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ” አለው።


“ሁሉን በቅ​ጽ​በት አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ ከዚህ ማኅ​በር መካ​ከል ፈቀቅ በሉ።”


እነ​ር​ሱም በግ​ን​ባ​ራ​ቸው ወድ​ቀው፥ “የነ​ፍ​ስና የሥጋ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ አንድ ሰው ኀጢ​አት ቢሠራ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በማ​ኅ​በሩ ላይ ይሆ​ና​ልን?” አሉ።


አጠ​ፋ​ቸው ዘንድ፥ ስማ​ቸ​ው​ንም ከሰ​ማይ በታች እደ​መ​ስስ ዘንድ ተወኝ፤ አን​ተ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ለሚ​በ​ረ​ታና እጅግ ለሚ​በዛ ሕዝብ አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ።’


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ ከተ​ቈ​ጣ​ባ​ችሁ ከቍ​ጣ​ውና ከመ​ዓቱ የተ​ነሣ ፈራሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያን ጊዜ ደግሞ ሰማኝ።


እርስ በርሳችሁ በኀጢአታችሁ ተናዘዙ። ትፈወሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለ ሌላው ይጸልይ፤ የጻድቅ ሰው ጸሎት በሥራዋ እጅግ ኀይል ታደርጋለች።


跟着我们:

广告


广告