Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 31:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ርሱ ጋር በሲና ተራራ የተ​ና​ገ​ረ​ውን በፈ​ጸመ ጊዜ ሁለ​ቱን የም​ስ​ክር ጽላት፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት የተ​ጻ​ፈ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ጽላት ለሙሴ ሰጠው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እግዚአብሔር በሲና ተራራ ላይ ለሙሴ መናገሩን ከፈጸመ በኋላ፣ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላት፣ ሁለቱን የምስክር ጽላት ለርሱ ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር ንግግሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች የሆኑ ሁለት የምስክር ጽላቶችን ሰጠው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እግዚአብሔርም ከሙሴ ጋር በሲና ተራራ የተናገረውን በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ጣት የተጻፈባቸውን ከድንጋይ የሆኑ ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ሰጠው።

参见章节 复制




ዘፀአት 31:18
17 交叉引用  

የን​ጉ​ሡ​ንም ልጅ አው​ጥቶ ዘው​ዱን ጫነ​በት፤ ምስ​ክ​ሩ​ንም ሰጠው፤ ቀብ​ቶም አነ​ገ​ሠው፥ “ንጉሡ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ” እያሉ በእ​ጃ​ቸው አጨ​በ​ጨቡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


ሙሴም ወደ ደመ​ናው ውስጥ ገባ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣ፤ ሙሴም በተ​ራ​ራው ላይ አርባ ቀን፥ አርባ ሌሊ​ትም ቈየ።


ጠን​ቋ​ዮ​ችም ፈር​ዖ​ንን፥ “ይህስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት ነው” አሉት፤ የፈ​ር​ዖን ልብ ግን ጸና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ አል​ሰ​ማ​ቸ​ውም።


ከእ​ነ​ዚያ ወራት በኋላ ከእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ጋር የም​ገ​ባው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ሕጌን በል​ቡ​ና​ቸው አኖ​ራ​ለሁ፤ በል​ባ​ቸ​ውም እጽ​ፈ​ዋ​ለሁ፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


እኔ ግን በእግዚአብሔር መንፈስ አጋንንትን የማወጣ ከሆንሁ፥ እንግዲህ የእግዚአብሔር መንግሥት ወደ እናንተ ደርሳለች።


እኔ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጣት አጋ​ን​ን​ትን የማ​ወጣ ከሆነ እን​ግ​ዲህ አሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት ወደ እና​ንተ ደር​ሳ​ለች።


እና​ንተ ራሳ​ች​ሁም በእኛ የተ​ላ​ከች የክ​ር​ስ​ቶስ መል​እ​ክት እንደ ሆና​ችሁ ያው​ቃሉ፤ ይህ​ቺ​ውም የተ​ጻ​ፈች በሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነው እንጂ በቀ​ለም አይ​ደ​ለም፤ በሥጋ ልብ ሠሌ​ዳ​ነት ነው እንጂ በድ​ን​ጋይ ሠሌ​ዳም አይ​ደ​ለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ራ​ራው ላይ በእ​ሳት መካ​ከል የተ​ና​ገ​ራ​ች​ሁን ዐሠ​ር​ቱን ቃላት ቀድሞ ተጽ​ፈው እንደ ነበረ በጽ​ላቱ ላይ ጻፈ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ር​ሱን ለእኔ ሰጠኝ።


ታደ​ር​ጉ​ትም ዘንድ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ቃል ኪዳን ዐሥ​ሩን ቃላት ነገ​ራ​ችሁ፤ በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በተ​ራ​ራው ላይ፤ በእ​ሳ​ትና በጨ​ለማ፥ በጭ​ጋ​ግና በዓ​ውሎ ነፋስ መካ​ከል ሆኖ በታ​ላቅ ድምፅ እነ​ዚ​ህን ቃሎች ለጉ​ባ​ኤ​ያ​ችሁ ሁሉ ተና​ገረ፤ ምንም አል​ጨ​መ​ረም። በሁ​ለ​ቱም የድ​ን​ጋይ ጽላት ላይ ጻፋ​ቸው፤ ለእ​ኔም ሰጣ​ቸው።


በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


跟着我们:

广告


广告