Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ወደ ግብፅ ንጉሥ ወደ ፈር​ዖን እሄድ ዘንድ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከግ​ብፅ ምድር አወጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሙሴ እግዚአብሔርን፣ “ወደ ፈርዖን የምሄድና የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ወደ ፈርዖን የምሄድና የእስራኤልንም ልጆች ከግብጽ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሙሴ ግን እግዚአብሔርን “ወደ ፈርዖን ሄጄ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ለማውጣት እኔ ማን ነኝ?” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሙሴም እግዚአብሔርን፦ “ወደ ፈርዖን የምሄድ የእስራኤልንም ልጆች ከግብፅ የማወጣ እኔ ማን ነኝ?” አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 3:11
13 交叉引用  

ንጉሡ ዳዊ​ትም ገባ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ምጦ እን​ዲህ አለ፥ “ጌታዬ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ ይህን ያህል የወ​ደ​ድ​ኸኝ እኔ ማን ነኝ? ቤቴስ ምን​ድን ነው?


አሁ​ንም አቤቱ አም​ላኬ ሆይ፥ እኔን ባሪ​ያ​ህን በአ​ባቴ በዳ​ዊት ፋንታ አን​ግ​ሠ​ኸ​ኛል፤ እኔም መው​ጫ​ዬ​ንና መግ​ቢ​ያ​ዬን የማ​ላ​ውቅ ታናሽ ብላ​ቴና ነኝ።


ስለ​ዚ​ህም ሰምቶ በሕ​ዝ​ብህ ላይ መፍ​ረድ ይችል ዘንድ፥ መል​ካ​ሙ​ንና ክፉ​ው​ንም ይለይ ዘንድ ለባ​ሪ​ያህ አስ​ተ​ዋይ ልቡና ስጠው፤ አለ​ዚ​ያማ በዚህ በታ​ላቅ ሕዝብ ላይ ይፈ​ርድ ዘንድ ማን ይች​ላል?”


ሁሉ ከአ​ንተ ዘንድ ነውና፥ ከእ​ጅ​ህም የተ​ቀ​በ​ል​ነ​ውን ሰጥ​ተ​ን​ሃ​ልና ይህን ያህል ችለን ልና​ቀ​ር​ብ​ልህ እኔ ማን ነኝ? ሕዝ​ቤስ ማን ነው?


ሙሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ሰ​ሙ​ኝም፤ እን​ዴ​ትስ ፈር​ዖን ይሰ​ማ​ኛል? እኔም አን​ደ​በተ ርቱዕ አይ​ደ​ለ​ሁም” ብሎ ተና​ገረ።


እኔም፥ “ወዮ​ልኝ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ እነሆ ሕፃን ነኝና እና​ገር ዘንድ አል​ች​ልም” አልሁ።


የሞት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸው ለሞት፥ የሕ​ይ​ወት መዓዛ የሚ​ገ​ባ​ቸ​ውም ለሕ​ይ​ወት ናቸው፤ ነገር ግን ይህ የሚ​ገ​ባው ማነው?


ኀይ​ላ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ሆነ ከእኛ ከራ​ሳ​ችን እንደ ሆነ አድ​ር​ገን ምንም ልና​ስብ አይ​ገ​ባ​ንም።


እር​ሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስ​ራ​ኤ​ልን በምን አድ​ና​ለሁ? ወገኔ በም​ናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂ​ቶች ናቸው፤ እኔም በአ​ባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው።


ዳዊ​ትም ሳኦ​ልን፥ “ለን​ጉሥ አማች እሆን ዘንድ እኔ ማን ነኝ? ሰው​ነ​ቴስ ምን​ድን ናት? የአ​ባ​ቴስ ወገን በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ምን​ድን ነው?” አለው።


跟着我们:

广告


广告