Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 አው​ራ​ንም በግ በሞ​ላው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ስለ ጣፋጭ ሽታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ረበ የእ​ሳት ቍር​ባን ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም አውራ በጉን በሙሉ በመሠዊያው ላይ አቃጥለው፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ጣፋጭ መዐዛና ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ መሥዋዕት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 አውራውን በግ በሙሉ በመሠዊያው ላይ ታቃጥለዋለህ፤ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ጣፋጭ ሽቱ ነው፤ ለጌታ የቀረበ የእሳት ቁርባን ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከዚያም በኋላ የአውራውን በግ ሥጋ በሙሉ ለእኔ ለእግዚአብሔር የምግብ መሥዋዕት አድርገህ አቃጥለው፤ ይህም መባ ሽታው እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 አውራውንም በግ በሞላው በመሠዊያው ላይ ታቃጥላለህ፤ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነው፤ ጣፋጭ ሽቱ ነው። ለእግዚአብሔር የቀረበ የእሳት ቍርባን ነው።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:18
23 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም ዐይ​ኖ​ቹን አቅ​ንቶ በተ​መ​ለ​ከተ ጊዜ፥ በኋ​ላው እነሆ፥ አንድ በግ ቀን​ዶቹ በዕፀ ሳቤቅ ተይዞ አየ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሄዶ በጉን ወሰ​ደው፤ በልጁ በይ​ስ​ሐቅ ፈን​ታም ሠዋው።


“የም​ት​ወ​ድ​ደ​ውን አንድ ልጅ​ህን ይስ​ሐ​ቅን ይዘህ ወደ ከፍ​ተ​ኛው ተራራ ሂድ፤ እኔም በም​ነ​ግ​ርህ በአ​ንድ ተራራ ላይ በዚያ መሥ​ዋ​ዕት አድ​ር​ገህ ሠዋው” አለው።


ይስ​ሐ​ቅም አባ​ቱን አብ​ር​ሃ​ምን ተና​ገ​ረው፥ “አባቴ ሆይ፥” አለ፤ እር​ሱም፥ “ልጄ፥ ምን​ድን ነው?” አለው። “እሳ​ቱና ዕን​ጨቱ ይኸው አለ፤ የመ​ሥ​ዋ​ዕቱ በግ ግን ወዴት አለ?” አለው።


ኖኅም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፥ ከን​ጹ​ሕም እን​ስሳ ሁሉ፥ ከን​ጹ​ሓን ወፎ​ችም ሁሉ ወሰደ፤ በመ​ሠ​ው​ያ​ውም ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን አቀ​ረበ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም መል​ካ​ሙን መዓዛ አሸ​ተተ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በልቡ አለ፥ “ምድ​ርን ዳግ​መኛ ስለ ሰዎች ሥራ አል​ረ​ግ​ምም፤ በሰው ልብ ከታ​ና​ሽ​ነቱ ጀምሮ ክፋት ሁል ጊዜ ይኖ​ራል፤ ደግ​ሞም ከዚህ ቀደም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁት ሕያ​ዋ​ንን ሁሉ እን​ደ​ገና አል​መ​ታም።


እሳ​ትም ከሰ​ማይ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወረ​ደች፤ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ እን​ጨ​ቱ​ንም፥ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም በላች፤ በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ያለ​ውን ውኃ፥ አፈ​ሩ​ንም ላሰች።


ገባ​ዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበ​ርና በዚያ መሥ​ዋ​ዕት ይሠዋ ዘንድ ተነ​ሥቶ ሄደ፤ ሰሎ​ሞ​ንም በዚያ መሠ​ዊያ ላይ በገ​ባ​ዖን አንድ ሺህ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።


ሐሤ​ት​ንና ደስ​ታን አሰ​ማኝ፥ የጻ​ድ​ቃን አጥ​ን​ቶች ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


አው​ራ​ው​ንም በግ በየ​ብ​ልቱ ትቈ​ር​ጠ​ዋ​ለህ፤ የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ ታጥ​ባ​ለህ፤ ከብ​ል​ቱና ከራ​ሱም ጋር ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።


ከእ​ጃ​ቸ​ውም ትቀ​በ​ለ​ዋ​ለህ፤ በመ​ሥ​ዊ​ያ​ውም ላይ ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ታቃ​ጥ​ለ​ዋ​ለህ፤ እርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።


“የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ታ​ችሁ ብዛት ለእኔ ምን​ድን ነው?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን የአ​ውራ በግ መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና የፍ​ሪ​ዳን ስብ ጠግ​ቤ​አ​ለሁ፤ የበ​ሬና የአ​ውራ ፍየ​ልም ደም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።


ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣ​ንን፥ ከሩ​ቅም ሀገር ቀረ​ፋን ታቀ​ር​ቡ​ል​ኛ​ላ​ችሁ? የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ች​ሁን አል​ቀ​በ​ለ​ውም፤ ቍር​ባ​ና​ች​ሁም ደስ አያ​ሰ​ኘ​ኝም።


ከክ​ን​ፎ​ቹም ይሰ​ብ​ረ​ዋል፤ ነገር ግን አይ​ለ​የ​ውም። ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያኖ​ረ​ዋል፤ መሥ​ዋ​ዕቱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍር​ባን ነው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹን ግን በውኃ ያጥ​ባሉ፤ ካህ​ኑም ሁሉን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል።


ስቡም ሁሉ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ፥ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ እርሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አው​ራ​ውን በግ ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን ነበረ።


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ስቡ​ንም በላ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው ተደ​ነቁ፤ በግ​ም​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።


በፍጹም ልብ በፍጹም አእምሮም በፍጹም ነፍስም በፍጹም ኀይልም እርሱን መውደድ፥ ባልንጀራንም እንደ ራስ መውደድ በሙሉ ከሚቃጠል መሥዋዕትና ከሌላው መሥዋዕት ሁሉ የሚበልጥ ነው፡” አለው።


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበ​ዛ​ል​ኝ​ማል፤ የመ​ዓዛ ሽታና የተ​ወ​ደደ መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን ስጦ​ታ​ች​ሁን ከአ​ፍ​ሮ​ዲጡ ተቀ​ብዬ አሟ​ል​ቻ​ለሁ።


ሳሙ​ኤ​ልም አንድ የበግ ጠቦት ወስዶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈጽሞ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት አድ​ርጎ ከሕ​ዝቡ ጋር አቀ​ረ​በው፤ ሳሙ​ኤ​ልም ስለ እስ​ራ​ኤል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው።


跟着我们:

广告


广告