Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 28:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 እን​ዲ​ሁም ኀጢ​አት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ እን​ዳ​ይ​ሞ​ቱም፥ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ሲገቡ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሲቀ​ርቡ በአ​ሮ​ንና በል​ጆቹ ላይ ይሆ​ናል፤ ለእ​ርሱ፥ ከእ​ር​ሱም በኋላ ለዘሩ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 አሮንና ወንድ ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንኳን በሚገቡበት ጊዜ ወይም በመቅደሱ ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ፣ በደል ፈጽመው እንዳይሞቱ እነዚህን መልበስ አለባቸው። “ለአሮንና ለትውልዶቹ ይህ የዘላለም ሥርዐት ይሆናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 ኃጢአት እንዳይሆንባቸውና እንዳይሞቱ፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ ወይም በመቅደሱ ሊያገለግሉ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናሉ፤ ለእርሱና ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘለዓለም ሥርዓት ይሆናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 አሮንና ልጆቹ ዘወትር ወደ ድንኳን ሲገቡ ወይም በተቀደሰው ስፍራ በክህነት ለማገልገል ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ ይለብሱታል፥ በዚህ ዐይነት የውስጥ ሰውነታቸው ስለማይጋለጥ ከሞት ይድናሉ፤ ይህ እንግዲህ ለአሮንና ለትውልዱ ሁሉ ጸንቶ የሚኖር ሥርዓት ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው እንዳይሞቱም፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል።

参见章节 复制




ዘፀአት 28:43
18 交叉引用  

ኀፍ​ረተ ሥጋህ በእ​ርሱ እን​ዳ​ይ​ገ​ለጥ ወደ መሠ​ዊ​ያዬ በደ​ረጃ አት​ውጣ።


በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ካለው መጋ​ረጃ ውጭ አሮ​ንና ልጆቹ ከማታ እስከ ማለዳ ድረስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያብ​ሩት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ለልጅ ልጃ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።


ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን በገቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይታ​ጠቡ፤ ይህም ለእ​ነ​ርሱ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።”


ወደ ውስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በር በገቡ ጊዜ የተ​ልባ እግር ልብስ ይል​በሱ፤ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በርና በቤቱ ውስጥ በአ​ገ​ለ​ገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አን​ዳች ነገር በላ​ያ​ቸው አይ​ሁን።


እን​ዳ​ይ​ሞ​ትም የጢሱ ደመና በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ያለ​ውን መክ​ደኛ ይሸ​ፍን ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዕጣ​ኑን በእ​ሳቱ ላይ ያደ​ር​ጋል።


መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ው​ንም ደግሞ ተከ​ት​ለው ላመ​ነ​ዘ​ሩ​ባ​ቸው ለሰ​ይ​ጣ​ናት አይ​ሠዉ። ይህ ለእ​ነ​ርሱ ለልጅ ልጃ​ቸው ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሁን።”


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትን፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ነገር አያ​ር​ክሱ።


ቢያ​ረ​ክ​ሱ​አት እን​ዳ​ይ​ሞቱ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ይ​ሸ​ከሙ፥ ሕግን ይጠ​ብቁ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


ስብና ደም እን​ዳ​ት​በሉ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ነው።”


“አንድ ሰው ቢበ​ድል፥ የሚ​ያ​ም​ለ​ው​ንም ቃል ቢሰማ፥ ምስ​ክ​ርም ሆኖ አንድ ነገር አይቶ እንደ ሆነ፥ ወይም ዐውቆ እንደ ሆነ ያነን ባይ​ና​ገር በደ​ሉን ይሸ​ከ​ማል፤


“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥


ለእ​ና​ንተ፥ በእ​ና​ን​ተም መካ​ከል ለሚ​ኖሩ መጻ​ተ​ኞች አንድ ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ ለልጅ ልጃ​ች​ሁም የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ናል፤ እና​ንተ እንደ ሆና​ችሁ እን​ዲሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መጻ​ተኛ ይሆ​ናል።


ከዚ​ህም በኋላ ለሞት የሚ​ያ​በቃ በደል እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን አይ​ግቡ።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም ከእ​ርሱ ባነ​ሣ​ችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ች​ሁም፤ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የቀ​ደ​ሱ​ትን አታ​ር​ክሱ።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ተና​ገ​ረው፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለእኔ የለ​ዩ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን ቍር​ባ​ኔን ሁሉ ትጠ​ብቁ ዘንድ ለአ​ንተ ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ ለአ​ንተ እስ​ክ​ታ​ረጅ፥ ከአ​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ።


ነገር ግን ንጹሕ የሆነ ሰው በመ​ን​ገ​ድም ላይ ያል​ሆነ ፋሲ​ካን ባያ​ደ​ርግ፥ ያ ሰው ከሕ​ዝቡ ዘንድ ተለ​ይቶ ይጠ​ፋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቍር​ባን በጊ​ዜው አላ​ቀ​ረ​በ​ምና ያ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።


跟着我们:

广告


广告