ዘፀአት 28:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃ ሮማኖችን አድርግ፤ በእነዚያም መካከል በዙሪያው በተመሳሳይ ቅርጽ የወርቅ ሮማኖች ሻኵራዎችን አድርግ፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 በጨርቁ ጠርዝ ዙሪያ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ ሮማኖቹን፣ በመካከሉም የወርቅ ሻኵራዎችን አብጅ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃ ሮማኖች አድርግ፤ በዚያም መካከል በዙሪያው የወርቅ ሻኩራዎች አድርግ፤ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 በታችኛው ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ የተሠሩ የሮማን ፍሬ ቅርጽ አድርግበት፤ በፍሬዎቹ መካከል ጣልቃ የሚገቡ ከወርቅ የተሠሩ ትናንሽ ቃጭሎች አድርግበት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 በታችኛውም ዘርፍ ዙሪያ ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ሮማኖች አድርግ፤ በዚያም መካከል በዙሪያው የወርቅ ሻኵራዎች አድርግ፤ 参见章节 |