Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 28:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 አሮ​ንም ወደ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም መታ​ሰ​ቢያ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ስሞች በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድዓ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸ​ከም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “አሮን ወደ መቅደሱ በሚገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርድ መስጫው ደረት ኪስ በልቡ ላይ ይሸከም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ ዘወትር መታሰቢያ እንዲሆን በጌታ ፊት የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ ደረት ኪስ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “አሮን ወደ ተቀደሰው ስፍራ ሲገባ የእስራኤል ነገዶች ስሞች የተቀረጹበትን ይህን የደረት ኪስ ይለብሳል፤ በዚህ ዐይነት እኔ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ሕዝቤን አስታውሳለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 አሮንም ወደ መቅደስ በገባ ጊዜ በእግዚአብሔር ፊት ለዘላለም መታሰቢያ የእስራኤልን ልጆች ስሞች በፍርዱ በደረት ኪስ ውስጥ በልቡ ላይ ይሸከም።

参见章节 复制




ዘፀአት 28:29
8 交叉引用  

ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም የመ​ታ​ሰ​ቢያ ድን​ጋ​ዮች ይሆኑ ዘንድ ሁለ​ቱን ዕን​ቍ​ዎች በል​ብሰ መት​ከፉ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ አሮ​ንም በሁ​ለቱ ጫን​ቃ​ዎች ላይ ለመ​ታ​ሰ​ቢያ ስማ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይሸ​ከ​ማል።


“ብልህ ሠራ​ተ​ኛም እን​ደ​ሚ​ሠራ የፍ​ር​ዱን ልብሰ እን​ግ​ድዓ ሥራው፤ እንደ ልብሰ መት​ከ​ፍም አሠ​ራር ሥራው፤ ከወ​ር​ቅና ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከጥሩ በፍ​ታም ሥራው።


ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ክፉ ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከል​ብሰ መት​ከ​ፉም እን​ዳ​ይ​ለይ፥ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ወደ ልብሰ መት​ከፉ ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል ያያ​ይ​ዙ​ታል።


በፍ​ርዱ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓም ውስጥ ኡሪ​ም​ንና ቱሚ​ምን ታደ​ር​ጋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ወደ ቤተ መቅ​ደስ በገባ ጊዜ በአ​ሮን ልብ ላይ ይሆ​ናሉ፤ አሮ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሁል​ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ፍርድ በልቡ ላይ ይሸ​ከ​ማል።


እንደ ቀለ​በት በል​ብህ፥ እንደ ቀለ​በ​ትም ማኅ​ተም በክ​ን​ድህ አኑ​ረኝ፤ ፍቅር እንደ ሞት የበ​ረ​ታች ናትና፥ ቅን​ዐ​ትም እንደ ሲኦል የጨ​ከ​ነች ናትና። ላን​ቃዋ እንደ እሳት ላንቃ እንደ ነበ​ል​ባል ነው።


አለ​ቃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ውስጥ ይሾ​ማል፤ ገዢ​አ​ቸ​ውም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይወ​ጣል፤ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔ ይመ​ለስ ዘንድ ልብ የሰ​ጠው ማን ነው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ወን​ድ​ሞች፥ የእ​ኔስ የልቤ ምኞት፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የማ​ቀ​ር​በው ጸሎ​ትም እስ​ራ​ኤል እን​ዲ​ድኑ ነው።


跟着我们:

广告


广告