Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 28:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ደግ​ሞም ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች ሥራ፤ በል​ብሰ መት​ከፉ ፊት ከጫ​ን​ቃ​ዎች በታች በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ከፉ ቋድ በላይ በመ​ጋ​ጠ​ሚ​ያው አጠ​ገብ ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶች አበጅተህ ከኤፉዱ መታጠቂያ ከፍ ብሎ ከመጋጠሚያው አጠገብ ካለው በኤፉዱ ፊት ለፊት፣ በትከሻ ላይ ካሉት ንጣዮች ግርጌ ጋራ አያይዘው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በተጨማሪም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ለፊት ከትከሻዎቹ በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቋድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ከነዚህም ሌላ ሁለት ተጨማሪ የወርቅ ቀለበቶች ሠርተህ ከፊት ለፊት በኩል በትከሻ ላይ ከሚወርዱት ከኤፉዱ ማንገቻዎች ጋር ከታች በኩል ታያይዘዋለህ፤ መያያዝ ያለበትም በስፌቱ መጋጠሚያ አጠገብና በብልኀት ከተጠለፈው መታጠቂያ በላይ በኩል ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ደግሞም ሁለት የወርቅ ቀለበቶች ሥራ፥ በኤፉዱም ፊት ከጫንቃዎች በታች በብልሃት ከተጠለፈ ከኤፉዱ ቍድ በላይ በመያዣው አጠገብ ታደርጋቸዋለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 28:27
3 交叉引用  

ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶ​ች​ንም ሥራ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ልብሰ መት​ከፉ በው​ስጥ በሚ​ያ​ል​ፍ​በት በከ​ን​ፈሩ በኩል በሁ​ለቱ የል​ብሰ እን​ግ​ድዓ ጫፎች ላይ ታኖ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውም በብ​ል​ሃት ከተ​ጠ​ለፈ ከል​ብሰ መት​ክፉ ቋድ በላይ እን​ዲ​ሆን፥ ከል​ብሰ መት​ከ​ፉም እን​ዳ​ይ​ለይ፥ ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከቀ​ለ​በ​ቶቹ ወደ ልብሰ መት​ከፉ ቀለ​በ​ቶች በሰ​ማ​ያዊ ፈትል ያያ​ይ​ዙ​ታል።


በላ​ዩም የተ​ጠ​ለ​ፈው የል​ብሰ መት​ከፍ ቋድ እንደ እርሱ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ይሁን፤ ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀይ ግም​ጃም ከተ​ፈ​ተለ፥ ከጥሩ በፍ​ታም የተ​ሠራ ይሁን።


跟着我们:

广告


广告