Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 25:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 በተ​ራራ ላይ እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ድ​ት​ሠራ ተጠ​ን​ቀቅ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 በተራራው ላይ በተገለጠልህ ምሳሌ መሠረት መሥራትህን ልብ በል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 በተራራው ላይ ባሳየሁህ ምሳሌ መሠረት ለመስራት ጥንቃቄ አድርግ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 በተራራው ላይ ባሳየሁህ ዕቅድ መሠረት ለመሥራት ጥንቃቄ አድርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ።

参见章节 复制




ዘፀአት 25:40
15 交叉引用  

ዳዊ​ትም ለመ​ቅ​ደሱ ወለል፥ ለቤ​ቱም፥ ለቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም፥ ለደ​ር​ቡና ለው​ስ​ጡም ጓዳ​ዎች፥ ለስ​ር​የ​ቱም መክ​ደኛ መቀ​መጫ ምሳ​ሌ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


ዕው​ቀት እንደ ተሰ​ጠው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤት ይሠራ ዘንድ ዳዊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ የተ​ጻ​ፈ​ውን ለልጁ ለሰ​ሎ​ሞን ሰጠው።


ዐሥ​ሩ​ንም የወ​ርቅ መቅ​ረ​ዞች እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው ሠራ፤ አም​ስ​ቱን በቀኝ፥ አም​ስ​ቱ​ንም በግራ በመ​ቅ​ደሱ ውስጥ አኖ​ራ​ቸው።


መቅ​ረ​ዙም፥ ዕቃ​ውም ሁሉ ከአ​ንድ መክ​ሊት ጥሩ ወርቅ ይሠሩ።


በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደ​ሪ​ያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃ​ውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠ​ራ​ለህ፤ እን​ዲሁ ትሠ​ራ​ለህ።


ድን​ኳ​ኑ​ንም በተ​ራ​ራው ላይ በአ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ ሥራ።


ሰሌ​ዳ​ውም ፍል​ፍል ይሁን፤ በተ​ራ​ራው እን​ዳ​ሳ​የ​ሁህ ምሳሌ እን​ዲሁ አድ​ርግ።


የሚ​ቀ​ቡ​ትን የቅ​ብ​ዐ​ቱ​ንም ዘይት፥ ለመ​ቅ​ደሱ የሚ​ያ​ጥ​ኑ​ትን ዕጣን እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሁሉ ያድ​ርጉ።”


ሙሴም ባስ​ል​ኤ​ል​ንና ኤል​ያ​ብን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን በል​ቡ​ና​ቸው ያሳ​ደ​ረ​ባ​ቸ​ው​ንና ጥበብ ያላ​ቸ​ውን፥ ሥራ​ው​ንም ለመ​ሥ​ራት ይቀ​ርብ ዘንድ ልቡ ያስ​ነ​ሣ​ውን ሁሉ ሥራ​ውን ሠር​ተው ይፈ​ጽሙ ዘንድ ጠራ​ቸው።


የመ​ቅ​ረ​ዝ​ዋም ሥራዋ እን​ዲህ ነበረ። ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ወርቅ የሆነ አፅ​ቆ​ችዋ ሥረ-ወጥ ነበሩ፤ አበ​ቦ​ች​ዋም ሁለ​ን​ተ​ና​ቸው ሥረ-ወጥ ነበሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ሳ​የው ምሳሌ መቅ​ረ​ዝ​ዋን እን​ዲሁ አደ​ረገ።


“ሙሴን ተና​ግሮ እንደ አዘ​ዘው በአ​ሳ​የው ምሳሌ የሠ​ራት የም​ስ​ክር ድን​ኳን በአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ዘንድ በም​ድረ በዳ ነበ​ረች።


እነ​ር​ሱም ሙሴ ድን​ኳ​ኒ​ቱን ሲሠራ ሳለ እንደ ተረዳ፥ ለሰ​ማ​ያዊ ነገር ምሳ​ሌና ጥላ የሚ​ሆ​ነ​ውን ያገ​ለ​ግ​ላሉ፤ “በተ​ራ​ራው እንደ ተገ​ለ​ጠ​ልህ ምሳሌ ሁሉን ታደ​ርግ ዘንድ ተጠ​ን​ቀቅ” ብሎት ነበ​ርና።


ኋላ ይህ በተ​ደ​ረገ ጊዜ ነገ ለእኛ ወይም ለት​ው​ል​ዳ​ችን ይህን ሲሉ፥ እኛ፦ እነሆ፥ አባ​ቶ​ቻ​ችን ያደ​ረ​ጉ​ትን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መሠ​ዊያ ምሳሌ እዩ፤ በእ​ኛና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው እንጂ ስለ​ሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ስለ ቍር​ባን አይ​ደ​ለም እን​ላ​ለን።


跟着我们:

广告


广告