Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 24:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሙሴም ወደ ደመ​ናው ውስጥ ገባ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣ፤ ሙሴም በተ​ራ​ራው ላይ አርባ ቀን፥ አርባ ሌሊ​ትም ቈየ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም ሙሴ ወደ ተራራው ሲወጣ ደመናው ውስጥ ገባ፤ በተራራውም ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ፤ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቆየ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሙሴም ወጥቶ በተራራው ላይ ወዳለው ደመና ውስጥ ገባ፤ እዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ፤ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀን አርባ ሌሊትም ቆየ።

参见章节 复制




ዘፀአት 24:18
18 交叉引用  

እር​ሱም አለ፥ “ነገ ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቁም። እነ​ሆም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ አለፈ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ትል​ቅና ብርቱ ነፋስ ተራ​ሮ​ቹን ሰነ​ጠቀ፤ ዓለ​ቶ​ቹ​ንም ሰባ​በረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በነ​ፋሱ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም። ከነ​ፋ​ሱም በኋላ የም​ድር መና​ወጥ ሆነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በም​ድር መና​ወጥ ውስጥ አል​ነ​በ​ረም።


ተነ​ሥ​ቶም በላ፤ ጠጣም፤ በዚ​ያም በበ​ላው የም​ግብ ኀይል እስከ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሲና ተራራ ላይ ወደ ተራ​ራው ራስ ወረደ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን ወደ ተራ​ራው ራስ ጠራው፤ ሙሴም ወጣ።


በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መታ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦


ሕዝ​ቡም ሙሴ ከተ​ራ​ራው ሳይ​ወ​ርድ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ፥ ወደ አሮን ተሰ​ብ​ስ​በው፥ “ይህ ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን ሰው ሙሴ ምን እንደ ሆነ አና​ው​ቅ​ምና ተነ​ሥ​ተህ በፊ​ታ​ችን የሚ​ሄዱ አማ​ል​ክት ሥራ​ልን” አሉት።


በዚ​ያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ነበረ፤ እን​ጀ​ራም አል​በ​ላም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣም። በጽ​ላ​ቱም ዐሥ​ሩን የቃል ኪዳን ቃሎች ጻፈ።


ሙሴም፥ “ለፈ​ር​ዖን ከከ​ተማ በወ​ጣሁ ጊዜ እጄን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆነች ታውቅ ዘንድ ነጐ​ድ​ጓዱ ጸጥ ይላል፤ በረ​ዶ​ውም፥ ዝና​ቡም ደግሞ አይ​ወ​ር​ድም።


ሙሴም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ከከ​ተማ ወጣ፤ እጁ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘረጋ፤ ነጐ​ድ​ጓ​ዱም፥ በረ​ዶ​ውም ጸጥ አለ፤ ዝና​ቡም በም​ድር ላይ አላ​ካ​ፋም።


አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።


በምድረ በዳም ከሰይጣን እየተፈተነ አርባ ቀን ሰነበተ፤ ከአራዊትም ጋር ነበረ፤ መላእክቱም አገለገሉት።


አርባ መዓ​ል​ትና አርባ ሌሊት ከዲ​ያ​ብ​ሎስ ተፈ​ተነ፥ በእ​ነ​ዚ​ያም ቀኖች ምንም አል​በ​ላም፤ እነ​ዚ​ያም ቀኖች ከተ​ፈ​ጸሙ በኋላ ተራበ።


“እኔም እንደ ፊተ​ኛው ጊዜ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በተ​ራ​ራው ላይ ቆምሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚህ ጊዜ ደግሞ ሰማኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ደም።


አንተ ግን በዚህ በእኔ ዘንድ ቁም፤ ርስት አድ​ርጌ በም​ሰ​ጣ​ቸው ምድር ላይ ያደ​ር​ጉ​አት ዘንድ የም​ታ​ስ​ተ​ም​ራ​ቸ​ውን ትእ​ዛ​ዜ​ንና ሥር​ዐ​ቴን፥ ፍር​ዴ​ንም ሁሉ እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


ስለ ሠራ​ች​ሁት ኀጢ​አት ሁሉ፥ እር​ሱ​ንም ለማ​ስ​ቈ​ጣት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ የሆ​ነ​ውን ነገር ስላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ፥ እንደ ፊተ​ኛው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ዳግ​መኛ ለመ​ንሁ፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፥ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


“እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ያጠ​ፋ​ችሁ ዘንድ ስለ ተና​ገረ ቀድሞ እንደ ለመ​ንሁ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለመ​ንሁ።


ሁለ​ቱን የድ​ን​ጋይ ጽላት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር የተ​ማ​ማ​ለ​ባ​ቸ​ውን የቃል ኪዳን ጽላት እቀ​በል ዘንድ ወደ ተራራ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በተ​ራ​ራው አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ተቀ​ምጬ ነበር፤ እን​ጀራ አል​በ​ላ​ሁም፤ ውኃም አል​ጠ​ጣ​ሁም።


跟着我们:

广告


广告