Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 24:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመ​ና​ውም ስድ​ስት ቀን ሸፈ​ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​መ​ናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመናውም ተራራውን እስከ ስድስት ቀን ድረስ ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን እግዚአብሔር በደመናው ውስጥ ሆኖ ሙሴን ጠራው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የጌታም ክብር በሲና ተራራ ላይ ተቀመጠ፥ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ዐረፈ፤ ደመናውም ተራራውን ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የእግዚአብሔርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ተቀመጠ፥ ደመናውም ስድስት ቀን ሸፈነው፤ በሰባተኛውም ቀን ከደመናው ውስጥ ሙሴን ጠራው።

参见章节 复制




ዘፀአት 24:16
14 交叉引用  

አሮ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማኅ​በር ሁሉ በተ​ና​ገረ ጊዜ ወደ ምድረ በዳ ፊታ​ቸ​ውን አቀኑ፤ እነ​ሆም፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር በደ​መ​ናው ታየ።


በሦ​ስ​ተ​ኛ​ውም ቀን ሕዝቡ ሁሉ ሲያዩ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ተራራ ላይ ይወ​ር​ዳ​ልና ለሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ተዘ​ጋ​ጅ​ተው ይጠ​ብቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን፥ “ከአ​ንተ ጋር ስነ​ጋ​ገር ሕዝቡ እን​ዲ​ሰሙ፥ ደግ​ሞም ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዲ​ያ​ም​ኑ​ብህ፥ እነሆ፥ በዐ​ምደ ደመና ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ” አለው። ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነገረ።


ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ እን​ግዳ በእ​ር​ስዋ ምንም ሥራ አት​ሥሩ፤


በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መታ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነበረ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ይመ​ጣል፤ በጽ​ዮን ተራራ ላይ ባለ ቦታ ሁሉ፥ በዙ​ሪ​ያ​ውም ላይ ደመና በቀን እንደ ጢስ፥ በሌ​ሊ​ትም እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠል የእ​ሳት ብር​ሃን ይጋ​ር​ዳል፤ በክ​ብ​ርም ሁሉ ላይ መጋ​ረጃ ይሆ​ናል።


በዝ​ናብ ቀን በደ​መና ውስጥ እንደ አለ ቀስተ ደመና አም​ሳያ፥ እን​ዲሁ በዙ​ሪ​ያው ያለ ፀዳል አም​ሳያ ነበረ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር ምሳሌ መልክ ይህ ነበረ። በአ​የ​ሁም ጊዜ በግ​ን​ባሬ ተደ​ፋሁ። የሚ​ና​ገ​ር​ንም ድምፅ ሰማሁ።


ሙሴና አሮ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ገቡ፤ ወጡም፤ ሕዝ​ቡ​ንም ባረኩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለሕ​ዝቡ ሁሉ ተገ​ለጠ።


ሙሴም፥ “ታደ​ር​ጉት ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዛ​ችሁ ቃል ይህ ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ይገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋል” አለ።


ማኅ​በሩ ሁሉ ግን “በድ​ን​ጋይ እን​ው​ገ​ራ​ቸው” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ተገ​ለጠ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ማኅ​በሩ በሙ​ሴና በአ​ሮን ላይ በተ​ሰ​በ​ሰቡ ጊዜ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ከበ​ቡ​አ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ ደመ​ናው ሸፈ​ናት፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ተገ​ለጠ።


በጨ​ለማ ውስጥ “ብር​ሃን ይብራ” ያለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ፊት የክ​ብ​ሩን ዕው​ቀት ብር​ሃን በል​ባ​ችን አብ​ር​ቶ​ል​ና​ልና።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


跟着我们:

广告


广告