Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 24:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሚ​መ​ስ​ላ​ቸው የሌለ የእ​ስ​ራ​ኤል ምር​ጦ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቦታ ታዩ፤ በሉም፤ ጠጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሆኖም እግዚአብሔር በእስራኤል ሕዝብ አለቆች ላይ እጁን አላነሣባቸውም። እግዚአብሔርን አዩ፣ በሉ፤ ጠጡም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በእስራኤል አዛውንቶች ላይ እጁን አልዘረጋም፤ እነርሱም እግዚአብሔርን አዩ፥ በሉም ጠጡም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር የእስራኤል መሪዎች የሆኑትን እነዚህን አረጋውያን ሰዎች አልቀሠፈም፤ ይልቁንም እግዚአብሔርን አይተው በፊቱ በሉ፤ ጠጡም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እጁንም በእስራኤል አዛውንቶች ላይ አልዘረጋም፤ እነርሱም እግዚአብሔርን አዩ፥ በሉም ጠጡም።

参见章节 复制




ዘፀአት 24:11
24 交叉引用  

አጋ​ርም ይና​ገ​ራት የነ​በ​ረ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራች፤ “አቤቱ የራ​ራ​ህ​ልኝ አንተ ነህ፤ የተ​ገ​ለ​ጠ​ል​ኝን በፊቴ አይ​ች​ዋ​ለ​ሁና።”


አብ​ር​ሃም በእ​ው​ነት ታላ​ቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆ​ና​ልና፤ የም​ድር ሕዝ​ቦ​ችም ሁሉ በእ​ርሱ ይባ​ረ​ካ​ሉና።


ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ።


አለ​ቆ​ችና ሕዝ​ቡም ሁሉ፥ “እንቢ በለው፤ እሺም አት​በ​ለው” አሉት።


የመቶ አለ​ቆ​ች​ንም፥ ከበ​ር​ቴ​ዎ​ች​ንም፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም አለ​ቆች፥ የሀ​ገ​ሩ​ንም ሕዝብ ሁሉ ወሰደ፤ ንጉ​ሡ​ንም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አወ​ረ​ዱት፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቤት በው​ስ​ጠ​ኛው በር በኩል ወደ ንጉሡ ቤት አመ​ጡት፤ ንጉ​ሡ​ንም በመ​ን​ግ​ሥቱ ዙፋን ላይ አስ​ቀ​መ​ጡት።


ጠባ​ቆች ግን ወዴት እንደ ሄድሁ፥ ምን እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁም አላ​ወ​ቁም ነበር፤ ለአ​ይ​ሁ​ድና ለካ​ህ​ናቱ፥ ለታ​ላ​ላ​ቆ​ችና ለሹ​ሞ​ቹም፥ ሥራም ይሠሩ ለነ​በ​ሩት ለሌ​ሎች እስ​ከ​ዚያ ጊዜ ገና አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም ነበር።


ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ፥ ለእ​ግ​ሮ​ቼም የወ​ጥ​መድ ገመ​ድን ዘረጉ፤ በመ​ን​ገ​ዴም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖሩ።


የሙሴ አማት ዮቶ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወሰደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እን​ጀራ ሊበሉ አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህ​ንም ለመ​ረ​ዳት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ለሕ​ዝቡ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “አንተ፥ አሮ​ንም፥ ናዳ​ብም፥ አብ​ዩ​ድም፥ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰባ ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ውጡ፤ በሩ​ቁም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስገዱ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና፦ ና እን​ጀ​ራ​ህን በደ​ስታ ብላ፥ በበጎ ልቡ​ናም የወ​ይን ጠጅ​ህን ጠጣ።


ታላ​ላ​ቆ​ች​ዋም ብላ​ቴ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ወደ ውኃ ሰደዱ፤ ወደ ጕድ​ጓድ መጡ፤ ውኃም አላ​ገ​ኙም፤ ዕቃ​ቸ​ው​ንም ባዶ​ውን መለሱ፤ ዐፈ​ሩም፤ ተዋ​ረ​ዱም፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ተከ​ና​ነቡ።


እኔ አፍ ለአፍ በግ​ልጥ እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ፤ በስ​ው​ርም አይ​ደ​ለም፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ክብር ያያል፤ አገ​ል​ጋዬ ሙሴን ማማ​ትን ስለ ምን አል​ፈ​ራ​ች​ሁም?” አለ።


“አለ​ቆች ቈፈ​ሩ​አት፥ በበ​ትረ መን​ግ​ሥት፥ በበ​ት​ራ​ቸ​ውም፥ የአ​ሕ​ዛብ ነገ​ሥ​ታት በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውና በግ​ዛ​ታ​ቸው አጐ​ደ​ጐ​ዱ​አት።”


በዚ​ያም በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ብሉ፤ እጃ​ች​ሁ​ንም በም​ት​ዘ​ረ​ጉ​በት፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በባ​ረ​ካ​ችሁ ነገር ሁሉ፥ እና​ን​ተና ቤተ​ሰ​ባ​ችሁ ደስ ይበ​ላ​ችሁ።


አንተ ከእ​ሳት መካ​ከል ሆኖ ሲና​ገር የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ እንደ ሰማ​ህና በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥


ማኑ​ሄም ሚስ​ቱን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አይ​ተ​ና​ልና ሞትን እን​ሞ​ታ​ለን” አላት።


በዚያ ጊዜ የቀ​ሩት ወደ ኀያ​ላ​ኑና ወደ ሕዝቡ ወረዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ እኔ በኀ​ያ​ላን ላይ ወረደ።


跟着我们:

广告


广告