ዘፀአት 23:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 የጠላትህን አህያ ከጭነቱ በታች ወድቆ ብታገኘው አትለፈው፤ ነገር ግን ከእርሱ ጋር ለማንሣት ርዳው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም5 የሚጠላህ ሰው አህያ፣ ጭነት ከብዶት ወድቆ ብታየው ርዳው እንጂ ትተኸው አትሂድ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው፥ ነገር ግን እንዲነሳ እርዳው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 የሚጠላህ ሰው አህያ ከጭነቱ ክብደት የተነሣ ወድቆ ብታገኝ፥ አህያውን ከወደቀበት ለማንሣት እንዲችል እርዳው እንጂ አልፈኸው አትሂድ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የሚጠላህን ሰው አህያ ከሸክሙ በታች ወድቆ ብታየው አትተወው፥ ነገር ግን ከእርሱ ጋር አንሣው። 参见章节 |