Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 23:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በም​ድ​ር​ህም መካን፥ ወይም የማ​ይ​ወ​ልድ አይ​ኖ​ርም፤ የዘ​መ​ን​ህ​ንም ቍጥር እሞ​ላ​ለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በምድርህም የሚያስወርዳት ወይም መካን ሴት አትኖርም፤ ረዥም ዕድሜም እሰጥሃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በምድርህ የምትጨነግፍ ወይም መካን አትኖርም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በምድርህ ፅንስ የሚያስወርዳት ወይም መኻን ሴት አትኖርም፤ ዕድሜህንም አረዝመዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በምድርህም መካን ወይም የምትጨነግፍ አትሆንም፤ የዘመንህን ቍጥር እሞላለሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 23:26
16 交叉引用  

አብ​ር​ሃ​ምም መል​ካም ሽም​ግ​ል​ናን ሸም​ግሎ፥ ዘመ​ኑ​ንም ፈጽሞ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ።


ይስ​ሐ​ቅም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜ​ንም ጠግቦ ሞተ፤ ወደ ወገ​ኖ​ቹም ተጨ​መረ፤ ልጆ​ቹም ዔሳ​ውና ያዕ​ቆብ ቀበ​ሩት።


ዳዊ​ትም በሸ​መ​ገለ ጊዜ፥ ዕድ​ሜ​ንም በጠ​ገበ ጊዜ ልጁን ሰሎ​ሞ​ንን በእ​ርሱ ፋንታ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አነ​ገ​ሠው።


በሬ​ዎ​ቻ​ቸው አይ​መ​ክ​ኑም፤ ላሞ​ቻ​ቸ​ውም አይ​ጨ​ነ​ግ​ፉም፤ በደ​ኅ​ናም ይወ​ል​ዳሉ።


ኢዮ​ብም ሸም​ግሎ ዕድ​ሜም ጠግቦ ሞተ።


በወ​ራቱ የደ​ረሰ አዝ​መራ እን​ዲ​ሰ​በ​ሰብ፥ የእ​ህሉ ነዶም በወ​ቅቱ ወደ አው​ድማ እን​ዲ​ገባ፥ በረ​ዥም ዕድሜ ወደ መቃ​ብር ትገ​ባ​ለህ።


መን​ግ​ሥ​ትህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሁሉ መን​ግ​ሥት ናት፥ ግዛ​ት​ህም ለልጅ ልጅ ነው።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ብም፥ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ወደ ቤትህ አይ​ገ​ባም።


ከዚ​ያም ወዲያ ጥቂት ዘመን ብቻ የሚ​ኖር ሕፃን፥ ወይም ዕድ​ሜ​ውን ያል​ፈ​ጸመ ሽማ​ግሌ አይ​ገ​ኝም፤ ጐል​ማ​ሳው የመቶ ዓመት ሆኖት ይሞ​ታ​ልና፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም የመቶ ዓመት ሆኖት የተ​ረ​ገመ ይሆ​ና​ልና።


አቤቱ! ስጣ​ቸው፤ ምን ትሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለህ? መካን ማኅ​ፀ​ንን፥ የደ​ረ​ቁ​ት​ንም ጡቶች ስጣ​ቸው።


የሆ​ድህ ፍሬ፥ የም​ድ​ር​ህም ፍሬ፥ የከ​ብ​ት​ህም ፍሬ፥ የላ​ም​ህም መንጋ፥ የበ​ግ​ህም መንጋ ቡሩክ ይሆ​ናል።


ለእ​ና​ንተ፥ ከእ​ና​ን​ተም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ችሁ መል​ካም ይሆን ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለዘ​ለ​ዓ​ለም በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዕድ​ሜ​አ​ችሁ ይረ​ዝም ዘንድ፥ እኔ ዛሬ የማ​ዝ​ዛ​ች​ሁን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ጠብቁ።”


ከአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ይልቅ የተ​ባ​ረ​ክህ ትሆ​ና​ለህ፤ ከሴ​ቶ​ችህ መካን አት​ኖ​ርም፤ ልጆች የሌ​ሏት አገ​ል​ጋ​ይም አት​ኖ​ርም፤ ከከ​ብ​ት​ህም መካን አይ​ኖ​ርም።


跟着我们:

广告


广告