Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 23:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የም​ድ​ር​ህን ፍሬ በኵ​ራት ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አምጣ። ጠቦ​ትን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 “የምድርህን ምርጥ ፍሬ በኵራት ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቤት አምጣ። “ጠቦት ፍየልን በእናቱ ወተት አትቀቅል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የመጀመሪያውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ ጌታ አምላክህ ቤት አምጣ፤ ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “በየዓመቱ ከምታመርቱት ምርት መጀመሪያ የደረሰውን በኲራት ወደ እኔ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጡ። “የበግን ወይም የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የተመረጠውን የምድርህን ፍሬ በኵራት ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣ። ጠቦትን በእናቱ ወተት አትቀቅል።

参见章节 复制




ዘፀአት 23:19
20 交叉引用  

በየ​ዓ​መ​ቱም የመ​ሬ​ታ​ች​ንን እህል ቀዳ​ም​ያት፥ የሁሉ ዓይ​ነት ዛፍ የፍሬ ቀዳ​ም​ያት ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት እና​መጣ ዘንድ፥


በሕ​ጉም እንደ ተጻፈ የል​ጆ​ቻ​ች​ን​ንና የእ​ን​ስ​ሶ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት፥ የበ​ሬ​ዎ​ቻ​ች​ን​ንና የበ​ጎ​ቻ​ች​ንን በኵ​ራት በአ​ም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት እና​መጣ ዘንድ፥


“ፈራ​ጆ​ችን አት​ስ​ደብ፥ የሕ​ዝ​ብ​ህ​ንም አለቃ ክፉ አት​ና​ገ​ረው።


የአ​ው​ድ​ማ​ህ​ንና የወ​ይ​ን​ህ​ንም መጀ​መ​ሪያ ለማ​ቅ​ረብ አት​ዘ​ግይ፤ የል​ጆ​ች​ህ​ንም በኵር ትሰ​ጠ​ኛ​ለህ።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውን የም​ድ​ር​ህን ፍሬ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ትወ​ስ​ዳ​ለህ። ጠቦ​ቱን በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።”


ጻድቅ ሰው ለእንስሳው ነፍስ ይራራል፤ የኃጥኣን ምሕረት ግን አለመመጽወት ነው።


እግዚአብሔርን በእውነት በአገኘኸው ሀብትህ አክብረው። ከእውነተኛ ፍሬህም ሁሉ ቀዳምያቱን አግባለት።


የአ​ሕ​ዛብ ልማድ ከንቱ ነውና፥ ከዱር በመ​ጥ​ረ​ቢያ እን​ደ​ሚ​ቈ​ረጥ፥ በሠ​ራ​ተ​ኛም እጅ እን​ደ​ሚ​ሠራ እን​ጨት ነው።


የበ​ኵ​ራቱ ሁሉ መጀ​መ​ሪያ ከየ​ዓ​ይ​ነቱ፥ ከቍ​ር​ባ​ና​ች​ሁም ሁሉ የማ​ን​ሣት ቍር​ባን ሁሉ ለካ​ህ​ናት ይሆ​ናል፤ በቤ​ታ​ች​ሁም ውስጥ በረ​ከት ያድር ዘንድ የአ​ዝ​መ​ራ​ች​ሁን ቀዳ​ም​ያት ለካ​ህ​ናቱ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


በካ​ህ​ና​ቱም ድን​በር አቅ​ራ​ቢያ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ዕጣ ለሌ​ዋ​ው​ያን ይሆ​ናል፤ ርዝ​መቱ ሁሉ ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ነውና ከእ​ርሱ ምንም አይ​ሸ​ጡም፤ አይ​ለ​ው​ጡ​ምም፤ የም​ድ​ሩም ቀዳ​ም​ያት አይ​ፋ​ለ​ስም።


መጀ​መ​ሪ​ያም ከም​ታ​ደ​ር​ጉት ሊጥ የተ​ለየ ቍር​ባን እስከ ልጅ ልጃ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል።


የበ​ከ​ተ​ዉን ሁሉ አት​ብሉ፤ ይበ​ላው ዘንድ በሀ​ገ​ርህ ደጅ ለተ​ቀ​መጠ መጻ​ተኛ ወይም ለባ​ዕድ ስጠው፤ አንተ ለአ​ም​ላ​ካህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ ነህና፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት በእ​ናቱ ወተት አት​ቀ​ቅል።


አሁ​ንም እነሆ፥ አቤቱ፥ አንተ የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ማርና ወተት የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን የም​ድ​ሪ​ቱን ፍሬ ቀዳ​ም​ያት አቅ​ር​ቤ​አ​ለሁ።


አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሚ​ሰ​ጥህ ምድር ከም​ት​ሰ​በ​ስ​በው ፍሬ ሁሉ ቀዳ​ም​ያት ውሰድ፤ በዕ​ን​ቅ​ብም አድ​ር​ገው፤ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስሙ ይጠ​ራ​በት ዘንድ ወደ መረ​ጠው ስፍራ ይዘህ ሂድ።


ከሴቶች ጋር ያልረከሱ እነዚህ ናቸው፤ ድንግሎች ናቸውና። በጉ ወደሚሄድበት የሚከተሉት እነዚህ ናቸው። ለእግዚአብሔርና ለበጉ በኵራት እንዲሆኑ ከሰዎች የተዋጁ እነዚህ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告