Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 23:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 “በዓ​መት ሦስት ጊዜ በዓል አድ​ር​ጉ​ልኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታከብራላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 “በዓመት ሦስት ጊዜ ለእኔ በዓልን ታደርግልኛለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 “እኔን የምታከብሩባቸው በዓመት ሦስት በዓላት ይኑሩአችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 በዓመት ሦስት ጊዜ በዓል ታደርግልኛለህ።

参见章节 复制




ዘፀአት 23:14
14 交叉引用  

ሰሎ​ሞ​ንም በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንና የሰ​ላ​ሙን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሠ​ራው መሠ​ዊያ ላይ ያሳ​ርግ ነበር፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ባለው መሠ​ዊያ ላይ ዕጣን ያሳ​ርግ ነበር፤ ቤቱ​ንም ጨረሰ።


ሙሴም እን​ዳ​ዘዘ እንደ ሥር​ዐ​ታ​ቸው በየ​ቀኑ ሁሉ፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ዎ​ቹም፥ በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​ዓ​መቱ ሦስት ጊዜ በየ​ቂ​ጣው በዓ​ልና በየ​ሰ​ባቱ ሱባዔ በዓል፥ በየ​ዳ​ሱም በዓል ቍር​ባን ያቀ​ርቡ ነበር።


በዓ​መት ሦስት ጊዜ በአ​ንተ ዘንድ ያለው ወንድ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይታይ።


ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን አማ​ል​ክት ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ።


“የቂ​ጣ​ውን በዓል ትጠ​ብ​ቀ​ዋ​ለህ። በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ወጥ​ተ​ሃ​ልና በታ​ዘ​ዘው ዘመን በሚ​ያ​ዝያ ወር እን​ዳ​ዘ​ዝ​ሁህ ሰባት ቀን ቂጣ ብላ።


“የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በየ​ክ​ብረ በዓሉ ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰ​ሜን በር በኩል ሊሰ​ግድ የሚ​ገ​ባው በደ​ቡብ በር በኩል ይውጣ፤ በደ​ቡ​ብም በር የሚ​ገ​ባው በሰ​ሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገ​ባ​በት በር አይ​መ​ለስ።


እስከ መጨ​ረ​ሻዋ ሰባ​ተኛ ሰን​በት ማግ​ስት ድረስ አምሳ ቀን ቍጠሩ፤ አዲ​ሱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅ​ርቡ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ በዚህ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን ጀምሮ ሰባት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳስ በዓል ይሆ​ናል።


እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዓ​ላት፥ በየ​ዘ​መ​ና​ቸው የም​ታ​ው​ጁ​አ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሱ ጉባ​ኤ​ያት ናቸው።


“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን ሲመሽ የእ​ግ​ዚ​እ​ብ​ሔር ፋሲካ ነው።


“በሚ​ያ​ዝያ ወር ከግ​ብፅ ሀገር በሌ​ሊት ወጥ​ተ​ሃ​ልና የሚ​ያ​ዝ​ያን ወር ጠብ​ቀህ፥ የአ​ም​ላ​ክህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፋሲካ አድ​ርግ።


በዓ​መት ሦስት ጊዜ በቂጣ በዓል፥ በሰ​ባቱ ሱባ​ዔም በዓል፥ በዳ​ስም በዓል ወንድ ልጅህ ሁሉ በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ረ​ጠው ስፍራ ይታይ፤


ያም ሰው በሴሎ ይሰ​ግድ ዘንድ፥ ለሠ​ራ​ዊት ጌታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይሠዋ ዘንድ ከከ​ተ​ማው ከአ​ር​ማ​ቴም በየ​ዓ​መቱ ይወጣ ነበር። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ካህ​ናት ሁለቱ የዔሊ ልጆች አፍ​ኒ​ንና ፊን​ሐስ በዚያ ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告