Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 22:25 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 “ከአ​ንተ ጋር ለተ​ቀ​መ​ጠው ለድ​ሃው ወገ​ንህ ብር ብታ​በ​ድ​ረው፥ አታ​ስ​ጨ​ን​ቀው፤ አራ​ጣም አታ​ስ​ከ​ፍ​ለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “ከሕዝቤ መካከል ችግረኛ ለሆነው ለአንዱ ገንዘብ ብታበድሩ፣ እንደ ዐራጣ አበዳሪ አትሁኑ፤ ወለድ አትጠይቁት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የባልንጀራህን ልብስ ለመያዣ ብትወስድ ፀሐይ ሳትገባ መልስለት፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 “በድኽነት ከሚኖሩት ሕዝቤ መካከል ለአንዱ እንኳ ገንዘብ ብታበድር፥ እንደ ገንዘብ አበዳሪ በመሆን ወለድ ጨምሮ እንዲከፍልህ አትጠይቀው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ከአንተ ጋር ለተቀመጠው ለወገኔ ለድሀው ገንዘብ ብታበድረው፥ እንደ ባለ አራጣ አትሁን፥ አራጣም አትጫንበት።

参见章节 复制




ዘፀአት 22:25
20 交叉引用  

ከነ​ቢ​ያ​ትም ልጆች የአ​ንዱ ሚስት የሆ​ነች አን​ዲት ሴት፥ “ባሌ ባሪ​ያህ ሞቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰው እንደ ነበረ አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ ባለ ዕዳም ሁለቱ ልጆ​ቼን ባሪ​ያ​ዎች አድ​ርጎ ሊወ​ስ​ዳ​ቸው መጥ​ቶ​አል” ብላ ወደ ኤል​ሳዕ ጮኸች።


መጥ​ታም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ነገ​ረ​ችው፤ እር​ሱም፥ “ሄደሽ ዘይ​ቱን ሽጭ ዕዳ​ሽ​ንም ክፈዪ፤ በተ​ረ​ፈ​ውም ዘይት የአ​ን​ቺ​ንና የል​ጆ​ች​ሽን ሰው​ነት አድኚ” አላት።


በል​ቤም አሰ​ብሁ፤ ታላ​ላ​ቆ​ቹ​ንና ሹሞ​ቹ​ንም፥ “ሁላ​ችሁ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወለድ ትወ​ስ​ዳ​ላ​ችሁ” ብዬ ተጣ​ላ​ኋ​ቸው፤ ትል​ቅም ጉባኤ ሰበ​ሰ​ብ​ሁ​ባ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።


እናቴ ሆይ! ለም​ድር ሁሉ የክ​ር​ክ​ርና የጥል ሰው የሆ​ን​ሁ​ትን እኔን ወል​ደ​ሽ​ኛ​ልና ወዮ​ልኝ! ለማ​ንም አል​ጠ​ቀ​ም​ሁም፤ ማንም እኔን አል​ጠ​ቀ​መ​ኝም፤ ከሚ​ረ​ግ​ሙ​ኝም የተ​ነሣ ኀይሌ አለቀ።


በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።


እጁ​ንም ከዐ​መፅ ቢመ​ልስ፥ አራ​ጣ​ንም አት​ርፎ ባይ​ወ​ስድ፥ ፍር​ዴ​ንም ቢያ​ደ​ርግ፥ በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ በአ​ባቱ ኀጢ​አት አይ​ሞ​ትም።


ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያ​ዣ​ውን ቢመ​ልስ፥ ፈጽ​ሞም ባይ​ቀማ፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ከል​ብሱ ቢያ​ለ​ብስ፤


በአ​ራጣ ባያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ባይ​ወ​ስድ፥ እጁ​ንም ከኀ​ጢ​አት ቢመ​ልስ፥ በሰ​ውና በሰው መካ​ከ​ልም የእ​ው​ነ​ትን ፍርድ ቢፈ​ርድ፥


በአ​ንቺ ውስጥ ደምን ያፈ​ስሱ ዘንድ መማ​ለ​ጃን ተቀ​በሉ፤ በአ​ን​ቺም አራ​ጣና ትርፍ ወስ​ደ​ዋል፤ ቀማ​ኛ​ነ​ት​ሽ​ንና ኀጢ​አ​ት​ሽን ፈጸ​ምሽ፤ እኔ​ንም ረሳ​ሽኝ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ልብ​ሳ​ቸ​ው​ንም አስ​ረው ለመ​ሥ​ዊ​ያው መጋ​ረጃ ያደ​ር​ጋሉ፤ በአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውም ቤት የቅ​ሚያ ወይን ጠጅ ይጠ​ጣሉ።


ስለዚህ ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ልትሰጠው በተገባህ ነበር፤ እኔም መጥቼ ያለኝን ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር።


ለምን ገን​ዘ​ቤን ወደ ለዋ​ጮች አላ​ስ​ገ​ባ​ህም? እኔም መጥቼ ከት​ርፉ ጋር በወ​ሰ​ድ​ሁት ነበር።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ጠህ ምድር ካሉ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲ​ትዋ ውስጥ ከሚ​ኖሩ ከወ​ን​ድ​ሞ​ችህ አንዱ ቢቸ​ገር ልብ​ህን አታ​ጽና፤ ለወ​ን​ድ​ምህ ከመ​ስ​ጠት እጅ​ህን አት​መ​ልስ።


ለብ​ሶት እን​ዲ​ተኛ እን​ዲ​ባ​ር​ክ​ህም ፀሐይ ሳይ​ገባ መያ​ዣ​ውን ፈጽ​መህ መል​ስ​ለት፤ በአ​ም​ላ​ክ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ምጽ​ዋት ይሆ​ን​ል​ሃል።


跟着我们:

广告


广告