Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 21:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ተነ​ሥ​ቶም በም​ር​ኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመ​ታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግ​ባ​ሩን ስላ​ስ​ፈ​ታው ገን​ዘብ ይክ​ፈ​ለው፤ ለባለ መድ​ኀ​ኒ​ትም ይክ​ፈ​ል​ለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በትሩንም ይዞ ደጅ ለደጅ የሚል ቢሆን፣ በዱላ የመታው ሰው አይጠየቅበትም፤ ሆኖም ለተጐጂው ሰው ለባከነበት ጊዜ ገንዘብ ይክፈል፤ ፈጽሞ እስኪድን ክትትል ያድርግለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ውጭ ቢወጣ፥ ሥራ ስላስፈታው ገንዘብ ከመክፈልና፥ እስኪፈወስም ድረስ ከማሳከም በቀር የመታው ሰው ከወንጀል ነጻ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በኋላም ተነሥቶ በትር እየተመረኰዘ መራመድ ቢቀጥል፤ ስለ ባከነበት ጊዜ የመታው ሰው ካሣ ይክፈለው፤ በደንብ እስከሚድንም ድረስ ተገቢውን እንክብካቤ ያድርግለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ተነሥቶም በምርኩዝ ወደ ሜዳ ቢወጣ፥ የመታው ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ተግባሩን ስላስፈታው ገንዘብ ይከፍለው ዘንድ፥ ያስፈውሰውም ዘንድ ግዴታ አለበት።

参见章节 复制




ዘፀአት 21:19
4 交叉引用  

በኢ​ዮ​አብ ራስ ላይና በአ​ባቱ ቤት ሁሉ ላይ ይም​ጣ​በት፤ በኢ​ዮ​አ​ብም ቤት ፈሳሽ ነገር ያለ​በት ወይም ለም​ጻም ወይም አን​ካሳ ወይም በሰ​ይፍ የሚ​ወ​ድቅ ወይም እን​ጀራ የሌ​ለው ሰው አይ​ታጣ።”


“ሁለት ሰዎ​ችም እርስ በር​ሳ​ቸው ቢጣሉ፥ አን​ዱም ሌላ​ውን በድ​ን​ጋይ ወይም በጡጫ ቢመታ፥ ያም ባይ​ሞት ነገር ግን በአ​ል​ጋው ላይ ቢተኛ፥


“ሰውም ወንድ ባሪ​ያ​ውን ወይም ሴት ባሪ​ያ​ውን በበ​ትር ቢመታ፥ በእጁ ቢሞ​ት​በ​ትም፥ ፈጽሞ ይቀጣ፤


የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ዳግመኛ ሽማግሌዎችና ባልቴቶች በኢየሩሳሌም አደባባይ ይቀመጣሉ፣ ሰውም ሁሉ ከዕድሜው ብዛት የተነሣ ምርኩዝ በእጁ ይይዛል።


跟着我们:

广告


广告