Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 20:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሕዝ​ቡም ሁሉ ነጐ​ድ​ጓ​ዱ​ንና መብ​ረ​ቁን፥ የቀ​ንደ መለ​ከ​ቱን ድምፅ፥ ተራ​ራ​ው​ንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ፈር​ተው ርቀው ቆሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሕዝቡም መብረቁንና ነጐድጓዱን የተራራውን መጤስና የመለከቱን ድምፅ ባዩና በሰሙ ጊዜ በፍርሀት ተንቀጠቀጡ፤ በርቀትም ቆሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ፈሩ ተንቀጠቀጡም፥ ርቀውም ቆሙ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሕዝቡም የነጐድጓዱንና የእምቢልታውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ እንዲሁም መብረቁ ሲብለጨለጭና ተራራው ሲጤስ ባዩ ጊዜ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ ርቀው ቆሙ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ባዩ ጊዜ ተርበደበዱ፥ ርቀውም ቆሙ።

参见章节 复制




ዘፀአት 20:18
13 交叉引用  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ፀሐ​ይም በገባ ጊዜ ነበ​ል​ባል መጣ፤ የእ​ሳት መብ​ራ​ትና የሚ​ጤስ ምድ​ጃም መጣ፤ በዚ​ያም በተ​ከ​ፈ​ለው መካ​ከል አለፈ።


አዳ​ምም አለ፥ “በገ​ነት ስት​መ​ላ​ለስ ድም​ፅ​ህን ሰማሁ፤ ዕራ​ቁ​ቴ​ንም ስለ​ሆ​ንሁ ፈራሁ፤ ተሸ​ሸ​ግ​ሁም።”


እና​ንተ ግን እንደ ሰው ትሞ​ታ​ላ​ችሁ፥ ከአ​ለ​ቆ​ችም እንደ አንዱ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ።


“እኔ ቅርብ አም​ላክ ነኝ እንጂ ሩቅ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ሁም ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በኮ​ሬብ በተ​ሰ​በ​ሰ​ባ​ች​ሁ​በት ቀን፦ ‘እን​ዳ​ን​ሞት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ደግሞ አን​ስማ፤ ይህ​ችን ታላቅ እሳት ደግሞ አንይ’ ብላ​ችሁ እንደ ለመ​ና​ች​ሁት ሁሉ።


ያስ​ተ​ም​ርህ ዘንድ ከሰ​ማይ ድም​ፁን አሰ​ማህ፤ በም​ድ​ርም ላይ ታላ​ቁን እሳት አሳ​የህ፤ ከእ​ሳ​ቱም መካ​ከል ቃሉን ሰማህ።


“እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በእ​ሳት መካ​ከል ድም​ፁን በሰ​ማ​ችሁ ጊዜ፥ ተራ​ራ​ውም በእ​ሳት ሲነ​ድድ እና​ንተ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች፥ ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ወደ እኔ ቀረ​ባ​ችሁ፤


አሁ​ንም አን​ሙት፤ ይህ​ችም ታላቅ እሳት አታ​ጥ​ፋን፤ እኛ የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ዳግ​መኛ ብን​ሰማ እን​ሞ​ታ​ለን።


አንተ ቅረብ፤ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ለ​ውን ሁሉ ስማ፤ እም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ንተ የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሁሉ ለእኛ ንገ​ረን፤ እኛም ሰም​ተን እና​ደ​ር​ገ​ዋ​ለን።


እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል እነ​ግ​ራ​ችሁ ዘንድ በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በእ​ና​ንተ መካ​ከል ቆሜ ነበር፤ እና​ንተ ከእ​ሳቱ ፊት ፈር​ታ​ች​ኋ​ልና፥ ወደ ተራ​ራው አል​ወ​ጣ​ች​ሁ​ምና። እር​ሱም አለ፦


跟着我们:

广告


广告