Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 20:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ም​ላ​ክህ ሰን​በት ናት፤ አንተ፥ ወንድ ልጅ​ህም፥ ሴት ልጅ​ህም፥ ሎሌ​ህም፥ ገረ​ድ​ህም፥ አህ​ያ​ህም፥ ከብ​ት​ህም፥ በደ​ጆ​ች​ህም ውስጥ ያለ እን​ግዳ በእ​ር​ስዋ ምንም ሥራ አት​ሥሩ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ሰንበት ነው። በዚያ ቀን አንተም ሆንህ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ አገልጋይህ ሆነ ሴት አገልጋይህ፣ ወይም እንስሳትህ፣ ወይም በደጅህ ያለ መጻተኛ ምንም ሥራ አትሠሩም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህ፥ ሴት ልጅህ፥ ወንድ ሠራተኛህ፥ ሴት ሠራተኛህ፥ ከብትህ፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ መጻተኛ ሁሉ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ማንም ሰው ሥራ አይሥራ፤ አንተም ሆንክ ልጆችህ፥ አገልጋዮችህም ሆኑ እንስሶችህ፥ በአገርህ ውስጥ የሚኖሩ መጻተኞችም ቢሆኑ ምንም ሥራ አትሥሩበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክህ ሰንበት ነው፤ አንተ፥ ወንድ ልጅህም፥ ሴት ልጅህም፥ ሎሌህም፥ ገረድህም፥ ከብትህም፥ በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፤

参见章节 复制




ዘፀአት 20:10
16 交叉引用  

የም​ድ​ር​ንም አሕ​ዛብ ሸቀ​ጥና ልዩ ልዩ እህል ሊገ​በዩ በሰ​ን​በት ቀን ቢያ​መጡ በሰ​ን​በት ወይም በተ​ቀ​ደ​ሰው ቀን ከእ​ነ​ርሱ አን​ገ​ዛም፤ ሰባ​ተ​ኛ​ው​ንም ዓመት እና​ከ​ብ​ራ​ለን፤ ከሰ​ውም ዕዳ ማስ​ከ​ፈ​ልን እን​ተ​ዋ​ለን።


ስድ​ስት ቀን ልቀ​ሙት፤ ሰባ​ተ​ኛው ቀን ግን ሰን​በት ነው፤ በእ​ርሱ አይ​ገ​ኝም” አለ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ ምል​ክት ነውና ሰን​በ​ቴን ፈጽሞ ጠብቁ።


“ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ታር​ፋ​ለህ። በም​ት​ዘ​ራ​በ​ትና በም​ታ​ጭ​ድ​በት ዘመን ታር​ፋ​ለህ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ታር​ፋ​ለህ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ የሚ​ሠ​ራ​በ​ትም ሁሉ ይሙት።


ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ከሚ​ቀ​መጡ መጻ​ተ​ኞች የሚ​ሆን፥ ከእኔ ተለ​ይቶ ጣዖ​ቶ​ቹን በልቡ የሚ​ያ​ኖር፥ የበ​ደ​ሉ​ንም መቅ​ሠ​ፍት በፊቱ የሚ​ያ​ቆም ሰው ሁሉ ስለ እኔ ይጠ​ይቅ ዘንድ ወደ ነቢዩ በመጣ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በራሴ እመ​ል​ስ​ለ​ታ​ለሁ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።


跟着我们:

广告


广告