Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 19:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ለሕ​ዝ​ቡም በዙ​ሪ​ያው ወሰን አድ​ር​ግ​ላ​ቸው፤ ወደ ተራ​ራው እን​ዳ​ት​ወጡ፥ ከእ​ርሱ ማን​ኛ​ው​ንም ክፍል እን​ዳ​ት​ነኩ ተጠ​ን​ቀቁ፤ ተራ​ራ​ው​ንም የነካ ፈጽሞ ይሞ​ታል” ብለህ ንገ​ራ​ቸው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በተራራው ዙሪያ ለሕዝቡ ወሰን አበጅተህ እንዲህ በላቸው፤ ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ወይም ግርጌውን እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ማንም ተራራውን ቢነካ በርግጥ ይሞታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ለሕዝቡም በዙሪያው ወሰን አድርግላቸው፥ እንዲህም በላቸው ‘ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውን የነካ ፈጽሞ ይሞታል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በተራራው ዙሪያ ድንበር አብጅ፤ እነርሱም ያንን ድንበር አልፈው ወደ ተራራው እንዳይወጡና እንዲያውም ድንበሩን እንዳይነኩ ንገራቸው፤ ማንም ሰው ከተወሰነው ድንበር አልፎ፥ ተራራውን ቢነካ በሞት ይቀጣ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ወሰንም ለሕዝቡ በዙሪያው አድርግላቸው፦ ወደ ተራራው እንዳትወጡ ጫፉንም እንዳትነኩ ተጠንቀቁ፤ ተራራውንም የነካ ፈጽሞ ይሞታል፤

参见章节 复制




ዘፀአት 19:12
11 交叉引用  

ፈር​ዖ​ንም ሙሴን፥ “ከእኔ ዘንድ ሂድ፤ በፊቴ በም​ት​ታ​ይ​በት ቀን ትሞ​ታ​ለ​ህና ዳግ​መኛ ፊቴን እን​ዳ​ታይ ተጠ​ን​ቀቅ” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ውረድ፤ ይህ​ንም ለመ​ረ​ዳት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ይ​ቀ​ርቡ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ብዙ እን​ዳ​ይ​ጠፉ ለሕ​ዝቡ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቃ​ቸው፤


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን፥ “ሕዝቡ ወደ ሲና ተራራ ይወጡ ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ አንተ፦ በተ​ራ​ራው ዙሪያ ወሰን አድ​ርግ፤ ቀድ​ሰ​ውም ብለህ አስ​ጠ​ን​ቅ​ቀ​ኸ​ኛ​ልና” አለው።


ሙሴም ብቻ​ውን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ረብ፤ እነ​ርሱ ግን አይ​ቅ​ረቡ፤ ሕዝ​ቡም ከእ​ነ​ርሱ ጋር አይ​ውጡ።”


በመ​ካ​ከ​ልህ ወጥ​መድ እን​ዳ​ይ​ሆ​ኑ​ብህ አንተ በም​ት​ገ​ባ​በት ምድር ከሚ​ኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ፤


ከአ​ን​ተም ጋር ማንም ሰው አይ​ውጣ፤ በተ​ራ​ራ​ውም ሁሉ ማንም አይ​ታይ፤ መን​ጎ​ችና ከብ​ቶ​ችም በዚያ ተራራ አጠ​ገብ አይ​ሰ​ማሩ።


ሕዝ​ቡ​ንም እን​ዲህ ብለህ እዘ​ዛ​ቸው፦ በሴ​ይር ላይ በተ​ቀ​መ​ጡት በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ በዔ​ሳው ልጆች ሀገር ታል​ፋ​ላ​ችሁ፤ እነ​ርሱ ይፈ​ሩ​አ​ች​ኋል፤ እን​ግ​ዲህ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።


“ለራ​ስህ ዕወቅ፤ ሰው​ነ​ት​ህን ፈጽ​መህ ጠብቅ፤ ዐይ​ኖ​ችህ ያዩ​ትን ይህን ሁሉ ነገር አት​ርሳ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ ከል​ቡ​ናህ አይ​ውጣ፤ ለል​ጆ​ች​ህና ለልጅ ልጆ​ች​ህም አስ​ተ​ም​ራ​ቸው።


ሊዳ​ሰስ ወደ​ሚ​ችል ወደ​ሚ​ቃ​ጠ​ልም እሳት ወደ ጭጋ​ግም፥ ወደ ጨለ​ማም ወደ ዐውሎ ነፋ​ስም፥


በእ​ና​ን​ተና በታ​ቦቱ መካ​ከል ያለው ርቀት በስ​ፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መን​ገድ በፊት አል​ሄ​ዳ​ች​ሁ​በ​ት​ምና የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ትን መን​ገድ እን​ድ​ታ​ውቁ ወደ ታቦቱ አት​ቅ​ረቡ።”


跟着我们:

广告


广告