Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 18:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ይህ​ንም ቃሌን ብታ​ደ​ርግ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ረ​ታ​ሃል፤ መፍ​ረ​ድም ትች​ላ​ለህ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በሰ​ላም ወደ ስፍ​ራው ይመ​ለ​ሳል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 አንተ ይህን ብታደርግና እግዚአብሔርም ይህንኑ ቢያዝዝህ፣ ድካምህን መቋቋም ትችላለህ፤ እነዚህም ሰዎች ሁሉ ረክተው ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ይህንም ብታደርግና፥ እግዚአብሔር ቢያዝዝህ፥ መቋቋም ትችላለህ፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው በሰላም ይሄዳል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚህ ዐይነት ብትሠራና ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ራስህን በከንቱ አታደክምም፤ ሕዝቡም በቀላሉ ጉዳዩ እየተፈጸመለት ወደየቤቱ ይሄዳል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ይህንም ብታደርግ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ቢያዝዝህ፥ መቆም ይቻልሃል፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይደርሳል።

参见章节 复制




ዘፀአት 18:23
15 交叉引用  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከአ​ብ​ር​ሃም ጋር ንግ​ግ​ሩን በጨ​ረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ።


ራሔ​ልም ዮሴ​ፍን ከወ​ለ​ደች በኋላ ያዕ​ቆብ ላባን እን​ዲህ አለው፥ “ወደ ስፍ​ራዬ፥ ወደ ሀገ​ሬም እመ​ለስ ዘንድ አሰ​ና​ብ​ተኝ።


እነ​ርሱ ግን “አንተ ከእኛ ከሁ​ላ​ችን ይልቅ እንደ ዐሥር ሽህ ሠራ​ዊት ስለ​ሆ​ንህ ብን​ሸሽ ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና፥ እኩ​ሌ​ታ​ች​ንም ብን​ሞት ልባ​ቸው አይ​ከ​ተ​ለ​ን​ምና አት​ውጣ፤ አሁ​ንም መር​ዳ​ትን ትረ​ዳን ዘንድ በከ​ተማ ብት​ኖ​ር​ልን ይሻ​ለ​ናል” አሉት።


ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ንጉ​ሡም ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገረ፤ ንጉ​ሡም ቤር​ዜ​ሊን አቅፎ ሳመው፤ መረ​ቀ​ውም፤ ወደ ስፍ​ራ​ውም ተመ​ለሰ።


የሶ​ር​ህ​ያም ልጅ አቢሳ አዳ​ነው፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ዊ​ው​ንም ወግቶ ገደ​ለው። ያን​ጊ​ዜም የዳ​ዊት ሰዎች፥ “አንተ የእ​ስ​ራ​ኤል መብ​ራት እን​ዳ​ት​ጠፋ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ከእኛ ጋር ለሰ​ልፍ አት​ወ​ጣም” ብለው ማሉ​ለት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ትን እንደ ሰጣ​ችሁ እዩ፤ ስለ​ዚህ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን የሁ​ለት ቀን እን​ጀራ ሰጣ​ችሁ፤ ሰው ሁሉ በቤቱ ይቀ​መጥ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማንም ከቤቱ አይ​ሂድ” አለው።


አንተ፥ ከአ​ን​ተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደ​ክ​ማ​ላ​ችሁ፤ ይህ ነገር ይከ​ብ​ድ​ብ​ሃል፤ አንተ ብቻ​ህን ልታ​ደ​ር​ገው አት​ች​ልም።


በሕ​ዝቡ ላይ ሁል ጊዜ ይፍ​ረዱ፤ የከ​በ​ዳ​ቸ​ውን ነገር ወደ አንተ ያም​ጡት፤ ቀላ​ሉን ነገር ሁሉ እነ​ርሱ ይፍ​ረዱ፤ ያቃ​ል​ሉ​ል​ሃል፤ ይረ​ዱ​ሃ​ልም።


ሙሴም የአ​ማ​ቱን ቃል ሰማ፤ እንደ አለ​ውም አደ​ረገ።


ሕዝ​ቡም እጅግ ታወኩ፤ ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስ​ንም ተከ​ራ​ከ​ሩ​አ​ቸው፤ ስለ​ዚህ ነገ​ርም ጳው​ሎ​ስ​ንና በር​ና​ባ​ስን፥ ጓደ​ኞ​ቻ​ቸ​ው​ንም በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ አሉት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትና ቀሳ​ው​ስት ሊል​ኳ​ቸው ተማ​ከሩ።


እንደ ተገ​ለ​ጠ​ል​ኝም ወጣሁ፤ በከ​ንቱ እን​ዳ​ል​ሮጥ፥ ወይም በከ​ንቱ ሮጬ እን​ዳ​ል​ሆነ፥ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል የም​ሰ​ብ​ከ​ውን ወን​ጌል አለ​ቆች መስ​ለው ለሚ​ታ​ዩት አስ​ታ​ወ​ቅ​ኋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሳሙ​ኤ​ልን፥ “ቃላ​ቸ​ውን ስማ፤ ንጉ​ሥም አን​ግ​ሥ​ላ​ቸው” አለው። ሳሙ​ኤ​ልም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች፥ “እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችሁ ወደ ከተ​ማ​ችሁ ሂዱ” አላ​ቸው።


跟着我们:

广告


广告