ዘፀአት 17:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፤ በበታቹም አኖሩ፤ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ተዘርግተው ነበር። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም12 የሙሴ እጆች እየዛሉ በሄዱ ጊዜ ድንጋይ ወስደው ከበታቹ አደረጉ፤ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በአንዱ በኩል ሌላውም በሌላ በኩል ሆነው እጆቹን ወደ ላይ ያዙ። ይኸውም እጆቹ ፀሓይ እስክትጠልቅ ድረስ ጸንተው እንዲቈዩ ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 የሙሴ እጆች ግን ዝለው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሑርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ያዙ፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ቀጥ አሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የሙሴ እጆች ስለ ዛሉ አሮንና ሑር ድንጋይ አምጥተው ሙሴ እንዲቀመጥበት አደረጉ፤ በግራና በቀኝ ክንዶቹን ደግፈው በመቆም ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ቈዩ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 የሙሴ እጆች ግን ከብደው ነበር፤ ድንጋይም ወሰዱ፥ በበታቹም አኖሩ፥ እርሱም ተቀመጠበት፤ አሮንና ሖርም አንዱ በዚህ አንዱ በዚያ ሆነው እጆቹን ይደግፉ ነበር፤ ፀሐይም እስክትገባ ድረስ እጆቹ ጠነከሩ። 参见章节 |