Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 16:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በ​ትን እንደ ሰጣ​ችሁ እዩ፤ ስለ​ዚህ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ቀን የሁ​ለት ቀን እን​ጀራ ሰጣ​ችሁ፤ ሰው ሁሉ በቤቱ ይቀ​መጥ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማንም ከቤቱ አይ​ሂድ” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እግዚአብሔር ሰንበትን የሰጣችሁ መሆኑን ልብ በሉ፤ በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚሆን እንጀራ የሰጣችሁ ለዚህ ነው። በሰባተኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ባለበት ይቈይ፤ ማንም አይወጣም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጌታ ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን ምግብ ሰጣችሁ፤ ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፤ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው አይውጣ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 እኔ አንድ የዕረፍት ቀን ሰጥቻችኋለሁ፤ ዘወትር በስድስተኛው ቀን ለሁለት ቀን የሚበቃ ምግብ ስለምሰጣችሁ በሰባተኛው ቀን እያንዳንዱ ሰው ከቤት ሳይወጣ፥ ባለበት ስፍራ ሁሉ ዕረፍት አድርጎ ይዋል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እግዚአብሔር ሰንበትን እንደ ሰጣችሁ እዩ፤ ስለዚህ በስድስተኛው ቀን የሁለት ቀን እንጀራ ሰጣችሁ፤ ሰው ሁሉ በስፍራው ይቀመጥ፥ በሰባተኛው ቀን ማንም ከስፍራው አይሂድ አለው። ሕዝቡም በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።

参见章节 复制




ዘፀአት 16:29
9 交叉引用  

የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ሰን​በ​ት​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝ​ንና ሥር​ዐ​ትን፥ ሕግ​ንም በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ትእ​ዛ​ዞ​ች​ንና ሕጎ​ችን ለመ​ስ​ማት እስከ መቼ እንቢ ትላ​ላ​ችሁ?


ሕዝ​ቡም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዐረፈ።


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእ​ኔና በእ​ና​ንተ ዘንድ ለልጅ ልጃ​ችሁ ምል​ክት ነውና ሰን​በ​ቴን ፈጽሞ ጠብቁ።


የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸ​ውም እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያውቁ ዘንድ፥ በእ​ኔና በእ​ነ​ርሱ መካ​ከል ምል​ክት ይሆኑ ዘንድ ሰን​በ​ታ​ቴን ሰጠ​ኋ​ቸው።


እኔ በስ​ድ​ስ​ተ​ኛው ዓመት በረ​ከ​ቴን በላ​ያ​ችሁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱም የሦ​ስት ዓመት ፍሬ ታፈ​ራ​ለች።


ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤


跟着我们:

广告


广告