Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 16:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ሙሴም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረ​ፍት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቀ​ደሰ ሰን​በት ነው፤ ነገ የም​ት​ጋ​ግ​ሩ​ትን ዛሬ ጋግሩ፤ የም​ት​ቀ​ቅ​ሉ​ት​ንም ቀቅሉ፤ የተ​ረ​ፈ​ው​ንም ሁሉ ለነገ እን​ዲ​ጠ​በቅ አኑሩ” አላ​ቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 እርሱም አላቸው፤ “እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ ‘ነገ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ሰንበት በመሆን፣ የዕረፍት ቀን ይሆናል።’ ስለዚህ መጋገር የምትፈልጉትን ጋግሩ፤ መቀቀል የምትፈልጉትን ቀቅሉ። የተረፈውን አስቀምጡ፤ እስከ ጧትም ድረስ አቈዩት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ የዕረፍት ሰንበት ነው፥ ለጌታ የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ተውት ለጥዋት ለእናንተ አስቀምጡት።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “የነገው ዕለት ለእርሱ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ ዛሬውኑ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈው ተከፍሎ ለነገ ይቀመጥ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱም፦ እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ ዕረፍት፥ ለእግዚአብሔርም የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ለነገ እንዲጠበቅ አኑሩት አላቸው።

参见章节 复制




ዘፀአት 16:23
16 交叉引用  

ወደ ሲናም ተራራ ወረ​ድህ፤ ከሰ​ማ​ይም ተና​ገ​ር​ሃ​ቸው፤ ቅኑን ፍር​ድና እው​ነ​ቱን ሕግ፥ መል​ካ​ሙ​ንም ሥር​ዐ​ትና ትእ​ዛዝ ሰጠ​ሃ​ቸው፤


የተ​ቀ​ደ​ሰ​ው​ንም ሰን​በ​ት​ህን አስ​ታ​ወ​ቅ​ሃ​ቸው፤ ትእ​ዛ​ዝ​ንና ሥር​ዐ​ትን፥ ሕግ​ንም በባ​ሪ​ያህ በሙሴ እጅ አዘ​ዝ​ሃ​ቸው።


ሙሴም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማንም ከእ​ርሱ አን​ዳች ለነገ አያ​ስ​ቀር” አላ​ቸው።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሁሉ ሥራ፤ በሬ​ህና አህ​ያህ ያርፉ ዘንድ ለባ​ሪ​ያ​ህም ልጅ ለመ​ጻ​ተ​ኛ​ውም ዕረ​ፍት ይሆን ዘንድ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ዕረፍ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ስች የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ናት፤ በሰ​ን​በት ቀን የሚ​ሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።


ከቤ​ቶ​ቻ​ችሁ በሰ​ን​በት ቀን ሸክ​ምን አታ​ውጡ፤ ሥራ​ንም ሁሉ አት​ሥሩ፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኋ​ቸው የሰ​ን​በ​ትን ቀን ቀድሱ።


ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ትሠ​ራ​ለህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን ግን የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ነው፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ጉባኤ ይሆ​ን​በ​ታል፤ ምንም ሥራ አት​ሠ​ሩም፤ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰን​በት ነው።


መና​ውም እንደ ድን​ብ​ላል ዘር ነበረ፤ መል​ኩም እንደ በረድ ነጭ ነበር።


ሕዝ​ቡም እየ​ዞሩ ይለ​ቅሙ ነበር፤ በወ​ፍ​ጮም ይፈ​ጩት፥ ወይም በሙ​ቀጫ ይወ​ቅ​ጡት፥ በም​ን​ቸ​ትም ይቀ​ቅ​ሉት ነበር፤ እን​ጎ​ቻም ያደ​ር​ጉት ነበር፤ ጣዕ​ሙም በዘ​ይት እንደ ተለ​ወሰ እን​ጎቻ ነበረ።


“ዕለተ ሰን​በ​ትን ጠብቅ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ዘ​ዘ​ህም ቀድ​ሳት።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


跟着我们:

广告


广告