ዘፀአት 16:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 የእስራኤልም ልጆች በአዩት ጊዜ እርስ በርሳቸው፥ “ይህ ምንድን ነው?” ተባባሉ። ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና። ሙሴም አላቸው፥ “ትበሉ ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ይህ ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እስራኤላውያንም ይህን ባዩ ጊዜ ምን እንደ ሆነ ባለማወቃቸው እርስ በርሳቸው፣ “ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ። ሙሴም፣ “ይህ ትበሉት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው አላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደሆነ አላወቁምና ሁሉም ሰው ወንድሙን፦ “ይህ ምንድነው?” በማለት ተጠያየቁ። ሙሴም፦ “እንድትበሉት ጌታ የሰጣችሁ ምግብ ነው።” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እስራኤላውያን ባዩት ጊዜ ምን እንደ ሆነ ባለማወቃቸው “ይህ ነገር ምንድን ነው?” በማለት እርስ በርሳቸው ተጠያየቁ። ሙሴም እንዲህ አላቸው፦ “ይህ እንድትበሉት እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 የእስራኤልም ልጆች ባዩት ጊዜ ያ ምን እንደ ሆነ አላወቁምና እርስ በእርሳቸው፦ ይህ ምንድር ነው? ተባባሉ። ሙሴም፦ ትበሉት ዘንድ እግዚአብሔር የሰጣችሁ እንጀራ ነው። 参见章节 |