Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 16:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ማን​ጐ​ራ​ጐር ሰማሁ፦ ማታ ሥጋን ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ ማለ​ዳም እን​ጀ​ራን ትጠ​ግ​ባ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ በላ​ቸው።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 “የእስራኤላውያንን ማጕረምረም ሰምቻለሁ፤ ይህን ንገራቸው፤ ‘ፀሓይ ከመጥለቋ በፊት ሥጋ ትበላላችሁ፤ ሲነጋም እንጀራ ትበላላችሁ፤ ከዚያም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ መሆኔን ታውቃላችሁ።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የእስራኤልን ልጆች ማጉረምረማቸውን ሰማሁ፦ እንዲህ በላቸው “ወደ ማታ ሥጋን ትበላላችሁ፥ ማለዳም እንጀራን ትጠግባላችሁ፤ እኔም ጌታ አምላካችሁ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 “እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ሰምቼአለሁ፤ ስለዚህ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘በዛሬው ምሽት ፀሐይ ከመጥለቅዋ በፊት ምግብ የሚሆናችሁን ሥጋ ታገኛላችሁ፤ በማለዳም የምትፈልጉትን ያኽል እንጀራ ታገኛላችሁ፤ በዚያን ጊዜም እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ እንደ ሆንኩ ታውቃላችሁ።’ ”

参见章节 复制




ዘፀአት 16:12
17 交叉引用  

የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ስለ አክዓብ ወደ ባሪ​ያው ወደ ኤል​ያስ መጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሕ​ዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥ ርስ​ቱ​ንም ተጸ​የፈ።


በዚ​ህም ወር እስከ ዐሥራ አራ​ተኛ ቀን ድረስ ጠብ​ቁት፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ማኅ​በር ሁሉ ሲመሽ ይረ​ዱት።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፦


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው አም​ላክ፥ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ፥ የይ​ስ​ሐ​ቅም አም​ላክ፥ የያ​ዕ​ቆ​ብም አም​ላክ እንደ ታየህ ያም​ኑ​ሃል” አለው።


ለእ​ኔም ሕዝብ እን​ድ​ት​ሆኑ እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፤ አም​ላ​ክም እሆ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን ባር​ነት ያወ​ጣ​ኋ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታው​ቃ​ለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወ​ን​ዙን ውኃ በእጄ ባለ​ችው በትር እመ​ታ​ለሁ፤ ውኃ​ውም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል።


በይ​ሁዳ ከተ​ሞ​ችና በሀ​ገሩ ሁሉ ከገ​በ​ሬ​ዎ​ችና መን​ጋን ይዘው ከሚ​ዞሩ ጋር የሚ​ኖሩ ሰዎች ይገ​ኛሉ።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው ከእ​ነ​ርሱ ጋር እን​ዳ​ለሁ፥ እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሕዝቤ እንደ ሆኑ ያው​ቃሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


ከዚች ቀን ጀምሮ ለዘ​ለ​ዓ​ለም የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ቸው እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


“እኔም በተ​ቀ​ደሰ ተራ​ራዬ በጽ​ዮን የም​ቀ​መጥ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም የተ​ቀ​ደ​ሰች ከተማ ትሆ​ና​ለች፥ እን​ግ​ዶ​ችም ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ል​ፉ​ባ​ትም።


እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና፤ ሰው​ነ​ታ​ች​ሁን ቀድሱ፤ ቅዱ​ሳ​ንም ሁኑ፤ እኔ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና፤


ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የተ​ቀ​ላ​ቀሉ ሕዝብ እጅግ ጐመጁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተቀ​ም​ጠው እን​ዲህ እያሉ አለ​ቀሱ፥ “ሥጋ ማን ያበ​ላ​ናል?


“የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ብ​ኝን እኒ​ህን ክፉ ማኅ​በር እስከ መቼ እታ​ገ​ሣ​ቸ​ዋ​ለሁ? ስለ እና​ንተ በእኔ ላይ የሚ​ያ​ጕ​ረ​መ​ር​ሙ​ትን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ማጕ​ረ​ም​ረ​ምን ሰማሁ።


跟着我们:

广告


广告